በክልሉ ከ240 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የሚገነቡ መናኸሪያዎች ተጠናቀው ለአገልግሎት ክፍት እንዲሆኑ በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ አስታወቀ
መናኸሪያዎቹ በ2 ወር ባልበለጠ ጊዜ ተጠናቀው ለህብረተሰቡ አገልግሎት እንዲሰጡ እንደሚሰራም ተገልጿል።
በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የመሰረተ ልማት ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ፋጅዮ ሳፒ እንደገለፁት፤ በክልሉ ባለፉት 6 ወራት በርካታ የመሠረተ ልማት ተግባራት ሲከናወኑ መቆየታቸውን ገልፀዋል።
የትራንስፖርት መሠረተ ልማትን ለማሳለጥ የክልል መንግስት ትኩረት ሰጥቶ ከሚሰራቸው ተግባራት መካከል በቀድሞ የደቡብ ክልል መንግስት የተጀመሩ የመንገድ፣ የድልድይና የመናኸሪያ ግንባታዎች ተጠቃሾች መሆናቸውን ኃላፊው አስረድተዋል።
እነዚህም የታረጫ 99፣ የቦንጋ 94 እና የሚዛን 56 በአጠቃላይ ከ249 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የመናኸሪያዎች ግንባታ እየተሰሩ እንደሚገኝ አቶ ፋጅዮ ተናግረዋል።
ከ3ቱም መናኸሪያዎች የታርጫና የሚዛን በአጭር ጊዜ ውስጥ እንደሚጠናቀቁ የገለፁት የቢሮ ኃላፊው፤ በተለያዩ ምክንያቶች የቦንጋ ሊቆይ የሚችል ቢሆንም ግንባታው በዚህ ዓመት ይጠናቀቃል ብለዋል።
ግንባታዎቹ በቀድሞ የደቡብ ክልል ተጀምረው ያልተጠናቀቁ በመሆናቸው የቢሮ ኃላፊዎች ከክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጋር እስከ ቦታው ድርስ በመጎብኘት ችግሮቹ እንዲፈቱ ሲደረግ መቆየቱን አቶ ፋጅዮ ገልጸዋል።
በተለይም የሚዛን መናኸሪያ ቦታውን ምቹ ለማድረግ ኮረት እየተደፋ እንደሚገኝና የመውጫ እና የመግቢያ ቦታዎች የመለየት ሥራ ተሰርተው በቅርቡ እንደሚጠናቀቅ የቢሮ ኃላፊው ተናግረዋል።
መናኸሪያዎቹ አገልግሎት መስጠት በሚጀምሩበት ወቅት ከትራንስፖርት ጋር ተያይዞ የሚስተዋሉ መጨናነቆች በእጅጉ እንደሚቀንሱም አቶ ፋጅዮ አብራርተዋል።
ዘጋቢ፡ አብዲሳ ዮናስ – ከሚዛን ጣቢያችን
More Stories
በወላይታ ዞን ባለፉት 10 ወራት ውስጥ ህገ-ወጥ ንግድና ለመከላከል በተደረገው ክትትል 2 ሺህ 135 ነጋዴዎች ላይ የእርምት እርምጃ መውሰድ መቻሉን የዞኑ ንግድና ገበያ ልማት መመሪያ አስታወቀ
በ2017/18 የመኸር አዝመራ ከ4 መቶ ሺ ሄክታር በላይ ማሳን በተለያዩ የሰብል ዓይነቶች መሸፈኑን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ግብርና ቢሮ አስታወቀ
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ የ2017 በጀት ዓመት የ10 ወራት አፈጻጸም እና የቀጣይ የክረምት ወራት ቅድመ ዝግጅት ግምገማ በሀላባ ቁሊቶ ከተማ እያካሄደ ይገኛል