ሀዋሳ፡ ጥር 22/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) በ2017 በጀት በመጀመሪያ ግማሽ አመት የተመዘገቡ አበረታች ዉጤቶችን በቀጣይ አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ አስታውቋል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ የ2017 በጀት ዓመት የሴክተሩን የ6 ወራት አጠቃላይ የስራ አፈጻጸምና ቀጣይ የ6 ወር ዕቅድ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ዉይይት እያካሄደ ይገኛል፡፡
በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት ዶ/ር ዋኖ ዋሎሌ እንደገለጹት፤ ሴክተሩ ባለፉት ስድስት ወራት በሁሉም ዞኖች በማህበራዊ ዘርፍ አረጋውያንን፣ አካል ጉዳተኞችን እና ተጋላጭ የህብረተሰብ ክፍሎች ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በርካታ ስራዎችን ማከናወኑን ጠቅሰው፣ በተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ አፈጻጸም ተመዝግቧል።
ቢሮዉ ለወጣቶች ጊዜያዊ የሥራ ዕድልን በመፍጠር ለውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት ዜጎችን በማሰልጠንና ሠላማዊ የኢንዱስትሪ ግንኙነትን በማረጋገጥ ውጤታማ ሥራዎች የሠራበት ጊዜ መሆኑንም አክለዋል።
በቀጣይም በግማሽ የበጀት ዓመቱ የተመዘገቡ የተሻሉ አፈጻጸሞችን አጠናክሮ ማስቀጠል እና የነበሩ ውስንነቶችን በመለየት በትኩረት ሊሰሩ እንደሚገባ የቢሮ ኃላፊው ተናግረዋል።
በውይይቱ ተሳታፊ የሆኑና የተሻለ አፈፃፀም ካስመዘገቡ ዞኖች ከመጡት መካከል ወ/ሮ ፍሬነሽ ሮባ እና አቶ ዋጂር እንዳሻዉ በበኩላቸው፤ ክልሉ ባስቀመጣቸው መመሪያዎች መሰረት ከዞን እስከ ታች በመውረድ የሃይማኖት ተቋማትን ጨምሮ ከሁሉም ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ሰፊ ስራ መስራታቸውን ተናግረው በቀጣይም የተሻለ አፈፃፀማቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉና ደካማ ጎናቸውን በመለየት እንደሚያሻሽሉ ተናግረዋል።
ዘጋቢ፡ ሰላምነሽ ፍቅሬ – ከጂንካ ጣቢያችን
More Stories
ቆሻሻን በአግባቡ በማስወገድ ከተማዋ ፅዱና ውብ እንድትሆን የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ ነው – የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች በቋሚነት የሚደገፉበት ስራ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የቡርጂ ዞን አስተዳደር አስታወቀ
“አንድ ሰው ወደዚህች ምድር ሲመጣ እንዲሰራ የተፈቀደለትና የሚጠበቅበት ነገር አለ” – ታደሰ ገብሬ /ጃክሰን/