በዞኑ “የአፈር ሀብታችን ለብልጽግናችን” በሚል መሪ ቃል ከጥር 22 ጀምሮ ለተከታታይ 45 ቀናት በዞኑ የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ሥራ እንደሚካሄድም ተገልጿል።
በዞኑ ከጪ ወረዳ የቺ ገዳ ንዑስ ተፋሰስ ዞናዊ በሆነው የማስጀመሪያ መርሀ ግብር የተገኙ አርሶአደሮች እንደሚሉት ባለፉት ዓመታት በለሙ የአፈርና ጥበቃ ሥራዎች አካባቢያቸው ተጠቃሚ መሆን ችሏል።
በተለይ ቀበሌያቸው በአፈር አሲዳማነት የተጠቃ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ የሚታየውን ችግር ለመፍታት የአፈርና ውኃ ጥበቃ ተግባርን በትጋት እንደሚወጡ ተናግረዋል።
የዳውሮ ዞን ግብርና፣ አካባቢ ጥበቃና ኅብረት ሥራ ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ በተላ በየነ እንደገለጹት በዞኑ የተፈጥሮ ሀብት መመናመን እና የአፈር መሸርሸርን ለመከላከል ከመቼውም ጊዜ በላይ የአፈርና ውኃ ጥበቃ ሥራዎች በትኩረት እየተከናወኑ ይገኛሉ።
የዘንድሮ 2017 ዓ.ም የተቀናጀ የማህበረሰብ ተፋሰስ ልማት የተፈጥሮ ሀብት መጠበቅ፣ ማልማትና በማቀናጀት ጥቅም ላይ ለማዋል በዘንድሮ የተፋሰስ ልማት ከ4 መቶ 8 ሺህ 8 መቶ 76 በላይ የማህበረሰብ ክፍሎችም በተግባሩ እየተሳተፉ ይገኛሉ ።
ለዕቅዱ መሳካት አስፈላጊዉ የዝግጅት ሥራዎች ከታህሣሥ አጋማሽ ጀምሮ የተከናወኑ ሲሆን ሥልጠና መስጠት፣ የልየታና የዲዛይን ስራ እንዲሁም የሰዉ ኃይልም ይሁን የመሳሪያ ልየታ በተገቢዉ መከናወኑንም አስረድተዋል።
በዳዉሮ ዞን ከጪ ወረዳ በማስጀመሪያ መርሀግብር የተገኙ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ቢሮ ተሳትፏዊ ግብርናና የአየር ንብረት ሽግግር ፕሮግራም ሥራ አስኪያጅ አቶ ታመነ ተስፋዬ በበኩላቸው ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ሥራ ካስገኘው ውጤት መነሻ በክልሉ 2 መቶ 25 ሺህ ሄክታር ማሣ በተለዩ 1 ሺህ 1 መቶ 90 ንዑስ ተፋሰሶች እንደሚለሙ ገልጸዋል።
በዳዉሮ ዞንም ወደ 40 ሄክታር የሚጠጋ ማሣ በነባር 3 መቶ 57 ንዑስ ተፋሰሶች እና 50 አዳዲስ ንዑስ ተፋሰሶች የሚለማ ሲሆን ከዘርፉ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሥነ ሕይወታዊና የጥበቃ ሥራዎች በትኩረት ሊሠራ እንደሚገባም አስረድተዋል።
ዘጋቢ ፡መሣይ መሠለ-ከዋካ ጣቢያችን
More Stories
ቆሻሻን በአግባቡ በማስወገድ ከተማዋ ፅዱና ውብ እንድትሆን የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ ነው – የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች በቋሚነት የሚደገፉበት ስራ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የቡርጂ ዞን አስተዳደር አስታወቀ
“አንድ ሰው ወደዚህች ምድር ሲመጣ እንዲሰራ የተፈቀደለትና የሚጠበቅበት ነገር አለ” – ታደሰ ገብሬ /ጃክሰን/