የዋቸሞ ዩኒቨርስቲ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ጋር በመተባበር በመንገድ ደህንነትና ትራፊክ ቁጥጥር ላይ ያተኮረ ስልጠና በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ እየተሰጠ ነው
ሀዋሳ፡ ጥር 22/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) የዋቸሞ ዩኒቨርስቲ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ጋር በመተባበር በመንገድ ደህንነትና ትራፊክ ቁጥጥር ላይ ያተኮረ ስልጠና በክልሉ ከሚገኙ ዞኖች፣ ልዩ ወረዳዎች እና ከተማ አስተዳደሮች ለተውጣጡ የትራፊክ ፖሊስ አስተባባሪዎች በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ እየተሰጠ ነው፡፡
በመድረኩ የተገኙት የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ኃላፊና የፕሬዝዳንቱ ተወካይ ዶክተር ካቻ አሰፋ እንደተናገሩት፤ የትራፊክ አደጋ ለበርካታ ዜጎች ህይወት መጥፋት መንስኤ ነው::
የትራፊክ አደጋ በማህበረሰቡ ላይ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ቀውሶችን እያስከተለ እንደሆነም ዶክተር ካቻ በመድረኩ ጠቅሰዋል::
በሀገራችን ደህንነቱ የተጠበቀ የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲኖር የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በተለይም የመንገድ ደህንነት ተቆጣጣሪዎች ትኩረት ሰጥተው እንዲሰሩ ዶክተር ካቻ መክረዋል::
በስልጠናው ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር እና የወንጀልና ትራፊክ አደጋ መከላከል ዘርፍ ኃላፊ ረዳት ኮሚሽነር አብርሃም ቲርካሶ፤ የትራፊክ አደጋ በሀገራችን አምራች የሆኑ ዜጎችን በመቅጠፍ ለተለያዩ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግር እየዳረገ ይገኛል ብለዋል::
የቁጥጥር ስርዓት ያለመዘመን ለትራፊክ አደጋ መከሰት መንስኤ እንደሆነም ምክትል ኮሚሽነር አብርሃም አመላክተዋል::
ፍጥነት፣ ግዴለሽነት፣ ጠጥቶ ማሽከርከርና የአሽከርካሪዎች ብቃት ማነስ ለትራፊክ አደጋ መከሰት ዋና ዋናዎቹ እንደሆኑም በመድረኩ ተጠቅሰዋል::
ዘጋቢ: በየነ ሰላሙ – ከሆሳዕና ጣቢያችን

More Stories
የአፍላ ወጣቶችና ወጣቶችን የስነ ተዋልዶ ጤና ችግሮች ለመቅረፍ የተጀመሩ ጥረቶችን ለማጎልበት የጤና አደረጃጀቶችን ሚና ማሳደግ እንደሚገባ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ አስታወቀ
ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የመግባት ዕድል ያገኙ ተማሪዎች የበለጠ ውጤታማ ለመሆን ትምህርታቸው ላይ ብቻ ሊያተኩሩ እንደሚገባ መልዕክት ተላለፈ
የሀዲያ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ለ2018 በጀት ዓመት ከ10 ቢልዮን ብር በላይ በጀት ለተለያዩ የልማት ስራዎች እንዲውል በተገቢው እንደሚሠራ ገለፀ