ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ከአድዋ ቀጥሎ ትልቁ አስተሳሳሪ የትርክት መገለጫ መሆኑ ተገለፀ
ቃልን በተግባር በህብረት ችለናል በሚል መሪ ቃል የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት መስኖና ቆላማ አካባቢ ልማት ቢሮ ሰራተኞችና አመራሮች የ2 መቶ 26 ሺህ ብር ቦንድ ግዢ ፈፅመዋል፡፡
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መስኖና ቆላማ አከባቢ ልማት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊና የመስኖ አስተዳደር ዘርፍ ኃላፊ አቶ ተመስገን ጥላሁን በበኩላቸው፤ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ከአድዋ ቀጥሎ ትልቁ አስተሳሳሪ የትርክት መገለጫ በመሆኑ የቢሮዉ ሰራተኞች አመራሮች እና በቢሮዉ ስር ያሉ ፕሮግራሞች በአጠቃላይ የ2 መቶ 26ሺ ብር ቦንድ ግዢ መፈፀማቸዉን ተናግረዋል፡፡
አክለዉም ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በግብርናዉ እና በኢንዱስትሪዉ ዘርፍ ከሚኖረዉ ጠቀሜታ ባሻገር ለጎረቤት ሀገራት የሚደረገዉ የኃይል ሽያጭ በሀገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ የሚያበረክተው አስተዋፅኦ ከፍተኛ እንደሆነም ገልፀዋል፡፡
እንደ አጠቃላይ የኢኮኖሚ ማሻሻያ ሪፎርም ሲደረግ ግብርና ዘርፍ ላይ ከነበረዉ ወደ ብዝሃ ዘርፍ የኢኮኖሚ ሃይልን በማጠናከር ዲጅታል ኢኮኖሚን ለመገንባት በሚደረጉ ሪፎርምች የኃይል አቅርቦት ስለሚያስፈልግ ሁሉንም አስተሳስሮ የያዘ ግድብ በመሆኑ እስከመጨረሻው ድረስ በተጀመረዉ ልክ ቀሪ ስራዎችን በመጨረስ የሀገራችንን ብልጽግና እናረጋግጣለን ሲሉም ኃላፊዉ ሀሳባቸዉን ሰጥተዋል፡፡
ከተቋሙ ሰራተኞች መካከል አቶ ማርከሻ ደጀኔ እና አዜብ ደጀኔ በሰጡት አስተያየት፤ የህዳሴ ግድብ ተገንብቶ እንዳይጠናቀቅ የነበሩ አሉባልታዎችና የዉጭ ጫናዎችን በመቋቋም ግድቡ ወደ መጠናቀቁ በመድረሱ ደስተኞች መሆናቸዉን ገልጸዉ ምንም አይነት የሀሳብ ልዩነቶች ቢኖሩም ሀገራዊ አጀንዳ በመሆኑ ሁሉም የበኩሉን አስተዋፅኦ ማበርከት እንዳለበት አሳስበዋል፡፡
ዘጋቢ፡ በናወርቅ መንግስቱ – ጂንካ ጣቢያችን

More Stories
አርባምንጭ ዩኒቨርስቲ ሳውላ ካምፓስ ለ9ኛ ጊዜ በተለያዩ የሙያ መስኮች ያሰለጠናቸውን 121 ተማሪዎችን አስመረቀ
ዲግሪው “ወረቀት ብቻ ሳይሆን፣ የሀገር ተስፋና የትውልድ ኃላፊነት ነው” – አፈወርቅ ካሱ (ፕ/ር)
በክልሉ የተጀመሩ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት የሚያሳድጉ ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው ጊዜ እንዲጠናቀቁ የድጋፍና ክትትል ስራ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ዶ/ር አስፋው ዲንጋሞ ገለጹ