የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንገዶች ባለስልጣን የተቋሙን የግማሽ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ከባለድርሻ አካላት ጋር እየገመገመ ይገኛል
ሀዋሳ፡ ጥር 22/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንገዶች ባለስልጣን የተቋሙን የግማሽ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ከባለድርሻ አካላት ጋር በወልቂጤ ከተማ እየገመገመ ነው።
በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንገዶች ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ምስጋናው ማቲዮስ፤ መድረኩ በበጀት አመቱ በመጀመሪያው ግማሽ አመት የነበሩ ጠንካራ ጎኖችን አጠናክሮ ለማስቀጠልና ውስንነቶችን ለመቅረፍ የሚያስችል መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በተለይም በዘርፉ የተያዙ ግቦችን ለማሳካት የሁሉም ባለድርሻ አካላት ቅንጅት ወሳኝ መሆኑን ገልፀዋል።
በመድረኩ አሁን ላይ የባለስልጣኑ እና የዲስትሪክቶች የ2017 በጀት አመት የግማሽ አመት አፈፃፀም ሪፖርት እየቀረበ ይገኛል፡፡
በመድረኩ ላይ የክልሉ መንገዶች ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ምስጋናው ማቲዮስን ጨምሮ የዲስትሪክቶች የስራ ሃላፊዎችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ፡፡
ዘጋቢ፡ ጅላሉ ፈድሉ – ከወልቂጤ ጣቢያችን
More Stories
ቆሻሻን በአግባቡ በማስወገድ ከተማዋ ፅዱና ውብ እንድትሆን የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ ነው – የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች በቋሚነት የሚደገፉበት ስራ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የቡርጂ ዞን አስተዳደር አስታወቀ
“አንድ ሰው ወደዚህች ምድር ሲመጣ እንዲሰራ የተፈቀደለትና የሚጠበቅበት ነገር አለ” – ታደሰ ገብሬ /ጃክሰን/