በዘንድሮው የአፈርና የውሃ ጥበቃ ስራ ከ3ሺ በላይ ሄክታር መሬት ለማልማት ታቅዶ ወደ ተግባር መገባቱን በስልጤ ዞን የስልጢ ወረዳ ግብርና ፅ/ቤት አስታወቀ
የአፈርና የውሃ ጥበቃ ስራ ያስገኘላቸውን ጥቅም በመረዳት በየአመቱ በንቃት በማሳተፍ አካባቢያቸውን እያለሙ መሆኑን በወረዳ አርሶአደሮች ተናግረዋል ።
“የተፈጥሮ ሀብት ልማት ስራችን ለብልፅግናችን” በሚል መሪ ቃል የተጀመረው የተፋሰስ ልማት ስራ በስልጤ ዞን ስልጢ ወረዳም የቅድማ ዝግጅት ስራ ተጠናቆ ወደ ተግባር መገባቱን የወረዳው ግብርና ፅህፈት ቤት ምክትልና ተፈጥሮ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሽፋ ነጃ ተናግረዋል።
ስራውን ውጤታማ ለማድረግ አስፈላጊው ቅድማ ዝግጅት የተደረጋ መሆኑን ያነሱት ኃላፊው ከመሰሪያና ከህብረተሰብ ልየታ ጀምሮ ባለሞያዎችና አርሶአደሮችን ማሰልጠን ተጠቃሾች ናቸው ብለዋል።
በዘንድሮው የአፈርና ውሃ ጥበቃ ልማት ስራ እንደ ወረዳው በተለዩ 25 ንዑስ ተፋሰሶች 3 ሺ15 ሄክታር መሬት እንደሚለማ ነው ኃላፊው የገለፁት::
በወረዳው ከዚህ በፊት የተሰራው የአፈርና የውሃ ጥበቃ ስራዎች የአፈር ለምነት ከመጠበቅ ጀምሮ የከርሰ ምድር ውሃና የደን ሽፋን በመሳደግ ረገድ ተጨባጭ ለውጥ መታየቱን ኃላፊው ገልፆዋል።
በጎርፍ የተጎዳና ገላጣማ የሆኑ መሬቶች መልሶ በማልማት ከአረንጓዴ ልማት ጋር በማስተሳሰር በተሰራው ስራ በወረዳው የደን ሽፋን እየጨመረ ከመምጣቱም ባለፈ ለንብ ማነብና መሰል የግብርና ስራዎችን ውጤታማነት ትልቅ ዕድል እየፈጠራ ነው ሲሉ ኃላፊው ገልፀዋል።
በወረዳው ያነጋገርናቸው አርሶ አደሮች ከዚህ በፊት የተሰራው የአፈርና የውሃ ጥበቃ ስራ ያስገኛላቸውን ጥቅም በመገንዘብ ዘንድሮ በነቂስ ወጥተው በማልማት ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል።
የአፈርና የውሃ ጥበቃ ስራው ምርትና ምርታማነትን ከመጨመር በተጨማሪ የክረምት ወቅት የሚፈጠረው የጎርፍ አደጋ ለመከላከል አይነተኛ መፍትሄ ነው ብለዋል ፡፡
ዘጋቢ:አሚና ጀማል-ከሆሳዕና ጣቢያችን

More Stories
የአፍላ ወጣቶችና ወጣቶችን የስነ ተዋልዶ ጤና ችግሮች ለመቅረፍ የተጀመሩ ጥረቶችን ለማጎልበት የጤና አደረጃጀቶችን ሚና ማሳደግ እንደሚገባ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ አስታወቀ
ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የመግባት ዕድል ያገኙ ተማሪዎች የበለጠ ውጤታማ ለመሆን ትምህርታቸው ላይ ብቻ ሊያተኩሩ እንደሚገባ መልዕክት ተላለፈ
የሀዲያ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ለ2018 በጀት ዓመት ከ10 ቢልዮን ብር በላይ በጀት ለተለያዩ የልማት ስራዎች እንዲውል በተገቢው እንደሚሠራ ገለፀ