በዳሎል ማዕከላዊ ዕዝ ስር የ101ኛ ሕዳሴ ኮር የሠራዊት አባላት በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌያት በድንገተኛ የመሬት መንሸራተት ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኞች መልሶ ማቋቋሚያ 820 ሺህ 400 ብር ድጋፍ አደረጉ
ድጋፉ በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የኮሩ ምክትል አዛዥ ኮሎኔል ኢያሱ ሀብቱ ገልጸዋል።
ኮሎኔል ኢያሱ ሀብቱ፤ አደጋው በደረሰበት ወቅት በተለያዩ ሀገራዊ ተልዕኮዎች ላይ እንደነበሩ ገልጸዉ የዕዙ ሰራዊት አባላት አሁንም ሰላም ከማስከበር ስራው ጎን ለጎን ህብረተሰቡን በተለያዩ መንገዶች እየደገፉ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
ድጋፉን የተረከቡት የጎፋ ዞን የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ታደለ ያዕቆብ፤ የሀገር መከላከያ ሠራዊት የኢትዮጵያ ሉአላዊነትና ዳር ድንበር እንዲከበር የሕይወት መስዋዕትነት እየከፈለ የኖረ የሀገር አለኝታ መሆኑን ተናግረዋል።
የኮሩ አመራሮችና አባላት ማህበራዊ ኃላፊነታቸውን በመወጣት በአደጋው የተፈናቀሉ የኅብረተሰብ ክፍሎችን በዘላቂነት ለማቋቋም ላደረጉት የገንዘብ ድጋፍ በዞኑ መንግስትና በተጎጂ ቤተሰቦች ስም አመስግነዋል።
ዘጋቢ: አወል ከድር – ከሳውላ ጣቢያችን
በዳሎል ማዕከላዊ ዕዝ ስር የ101ኛ ሕዳሴ ኮር የሠራዊት አባላት በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌያት በድንገተኛ የመሬት መንሸራተት ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኞች መልሶ ማቋቋሚያ 820 ሺህ 400 ብር ድጋፍ አደረጉ

More Stories
የአፍላ ወጣቶችና ወጣቶችን የስነ ተዋልዶ ጤና ችግሮች ለመቅረፍ የተጀመሩ ጥረቶችን ለማጎልበት የጤና አደረጃጀቶችን ሚና ማሳደግ እንደሚገባ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ አስታወቀ
ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የመግባት ዕድል ያገኙ ተማሪዎች የበለጠ ውጤታማ ለመሆን ትምህርታቸው ላይ ብቻ ሊያተኩሩ እንደሚገባ መልዕክት ተላለፈ
የሀዲያ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ለ2018 በጀት ዓመት ከ10 ቢልዮን ብር በላይ በጀት ለተለያዩ የልማት ስራዎች እንዲውል በተገቢው እንደሚሠራ ገለፀ