ሀዋሳ፡ ጥር 20/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመታገዝ በበጋ መስኖ ስራ ተሰማርተው በመስራታቸው ተጠቃሚነታቸውን እያረጋገጡ መሆናቸውን በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሀድያ ዞን የሶሮ ወረዳ አርሶ አደሮች ተናግረዋል፡፡
የአርሶ አደሮችን የማልማት አቅም ለማሳደግና ተጠቃሚነታቸውን ይበልጥ ለማረጋገጥ በበጋ መሥኖ ስራ ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን የወረዳው ግብርና ጽ/ቤት አስታውቋል፡፡
በሀድያ ዞን ሶሮ ወረዳ በበጋ መስኖ ስራ የተሰማሩ የጊዳቸሞና ሁለተኛ ሃንቆታ ቀበሌ አርሶ አደሮች እንደተናገሩት፤ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም በበጋ መስኖ የተለያዩ የጓሮ አትክልቶችን እያለሙ ውጤታማ ሆነዋል::
የበጋ መስኖ ስራ ከጀመሩ ወዲህ የምግብ ዋስትናቸውን ከማረጋገጥ አልፎ ለገበያ ጭምር እያቀረቡ እንደሆነም አርሶ አደሮቹ ጠቁመዋል::
በዘርፉ የበለጠ ውጤታማ ለመሆን ግብአት አቅርቦት ላይ የሚታየውን ችግር ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት እንዲፈቱ ጠይቀዋል።
በሀድያ ዞን ሶሮ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ ተመስገን ዳጌቦ በበኩላቸው፤ በወረዳው በዘንድሮ በበጋ መስኖ ልማት 3ሺህ 3 መቶ በላይ ሄክታር መሬት ለማልማት ታቅዶ በእስካሁን ባለው ሂደት 3ሺህ 2መቶ 65 ሄክታር መሬት በተለያዩ አዝዕርቶች እየለማ እንደሚገኝ ጠቁመዋል፡፡
ለአርሶ አደሮቹ የገበያ ትሥሥር በመመቻቸቱ ይበልጥ ተጠቃሚ እንዲሆኑ በትኩረት እየተሰራ መሆኑንም ምክትል ኃላፊው አመላክተዋል።
አርሶ አደሮቹ ዘመናዊ የበጋ መስኖ በመጠቀም በርበሬ፣ ሽንኩርት እና ስንዴ እያለሙ መሆናቸውንም አቶ ተመስገን ገልጸዋል።
የግብአት አቅርቦት ችግሮችን ለመፍታት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅርበት እየተሰራ መሆኑንም ጠቅሰዋል::
ዘጋቢ፡ አብርሃም ሙጎሮ – ከሆሳዕና ጣቢያችን
More Stories
ቆሻሻን በአግባቡ በማስወገድ ከተማዋ ፅዱና ውብ እንድትሆን የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ ነው – የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች በቋሚነት የሚደገፉበት ስራ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የቡርጂ ዞን አስተዳደር አስታወቀ
“አንድ ሰው ወደዚህች ምድር ሲመጣ እንዲሰራ የተፈቀደለትና የሚጠበቅበት ነገር አለ” – ታደሰ ገብሬ /ጃክሰን/