ዳራሮና መሰል በዓላት በማስተዋወቅና ለማሳደግ በሚደረገው ርብርብ የሴቶች ተሳትፎ ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው ተጠቆመ

ዳራሮና መሰል በዓላት በማስተዋወቅና ለማሳደግ በሚደረገው ርብርብ የሴቶች ተሳትፎ ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው ተጠቆመ

ሀዋሳ፣ ጥር 17/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) የበዓሉ ተሳታፊ ሴቶችም በበኩላቸው ለዳራሮ በዓል አስፈላጊውን ዝግጅት በማድረግ የበኩላቸውን ሲወጡ መቆየታቸውን ተናግረዋል፡፡

በወረዳው በምችሌ ግርሳ ሶንጎ በተከበረው በብሔሩ ዘመን መለወጫ ዳራሮ አግኝተን ካነጋገርናቸው ሴቶች መካከል ወ/ሮ መብራት ፊጋ፣ መሪኩር ወልደየስና ባዩሽ ሽፈራው ሴቶች ከጥር ወር መግብያ ጀምሮ የተለያዩ ዝግጅት በማከናወን ለበዓሉ ድምቀት የበኩላቸውን ሲወጡ መቆየታቸውን ተናግረዋል፡፡

ዳራሮ በዓል ከዝግጅት ምዕራፍ ጀምሮ ቡራቶ፣ ቦካ መጠጥ፣ ዳራሮና ሌሎች የምግብ ዓይነቶች በመስራት እንግዶችን በማስተናገድ የድርሻቸውን በመወጣት ላይ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡

ይህንን የማንነት መገለጫ የሆነ ዳራሮንና መሰል በዓላትን ለትውልድ በማስተዋወቅ ላይ መሆናቸውንም ሴቶቹ ጠቁመዋል፡፡

የዲላ ዙሪያ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታርኩ ታደሰ በወረዳው በተከበረው በዳራሮ በዓል ባስተላለፉት መልዕክት፤ ዳራሮ በዓል አክብርን ብቻ ወደየቤታችን የምንመለሰው ሳይሆን ከአባጋዳ ለአመቱ የሚሆን መተዳደሪያ አዋጅ የሚያስተላልፉበት በዓል ነው ብለዋል፡፡

አያይዘውም አስተዳዳሪው ሴቶች ለበዓሉ ድምቀት ከዋዜማው ጀምሮ በርካታ ተግባራት ሲያከናውኑ መቆየታቸውን በመጠቆም ወጣቱ ትውልድና ሴቶች በዓሉን ለማስተዋወቅና ለማሳደግ የበኩላቸውን እየተወጡ መሆናቸውንም አብራርተዋል፡፡

የዞኑ አስተዳዳሪ ተወካይና ኢንቨስትመንት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ደመላሽ ብሬ በበኩላቸው ዳራሮ የሠላም፣ የፍቅርና የአንድነት በዓል በመሆኑ የእርስ በእርስ ትስስር በማጠናከር ዳራሮን በተግባር ማሳየት መቻል አለብን ሲል ገልፀዋል፡፡

አክለውም ወቅቱ ለተለያዩ ለእርሻ ሥራዎች ዝግጅት የሚፈጸምበት በመሆኑ ህብረተሰቡ ለልማትና ቁጠባ ትኩረት ሰጥቶ እንዲረባረቡ አሳስበዋል፡፡

ዘጋቢ፦ እምነት ሽፈራው – ከይርጋጨፌ ጣቢያችን