በፍትህ ተቋማት የሚስተዋሉ ክፍተቶችን ለማረም የአሰራር ስልቶችን ከመቀየስ ባሻገር ሪፎርሙን በውጤታማነት መተግበር እንደሚያስፈልግ ተገለፀ
ሀዋሳ፣ ጥር 17/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) በፍትህ ተቋማት የሚስተዋሉ ክፍተቶችን ለማረም የአሰራር ስልቶችን ከመቀየስ ባሻገር ሪፎርሙን በውጤታማነት መተግበር እንደሚያስፈልግ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ጸሐይ ወራሳ አስገነዘቡ።
የክልሉ መንግስት የፍትህ ትራንስፎርሜሽን ተግባራት የስድስት ወር አፈጻጸም ግምገማ መድረክ በሳውላ ከተማ ተካሂዷል።
በመድረኩ የተገኙት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ፀሐይ ወራሳ እንደገለጹት ከዚህ ቀደም በፍትህ ስርዓቱ የነበሩ ክፍተቶችን ለማረምና የፍትህ ተደራሽነትን ለማሳደግ የፍርድ ቤቶችና የፍትህ አካላት ሪፎርም ቁልፍ ሚና ስላለው የፍትህ ተቋማት ለዘርፉ ትኩረት በመስጠት የህዝቡን እርካታ ማሳደግ እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።
በዘርፉ የሚስተዋለውን የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራት ከማሳደግ ባሻገር ቅሬታዎችን ለመፍታት ሪፎርሙን በበላይነት የሚመራው የስትሪን ኮሚቴ አባላት ከፍተኛ ሀላፊነት እንዳለባቸው አሳስበዋል።
እንደ ሀገር የተጀመረውን ለውጥ ለማስቀጠለ የአሰራር ስልት በመቀየስ በፍትህ ተቋማት ላይ የሚነሱ ችግሮችን ፈጥኖ ማረም እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል።
በታማኝነት፣ ህግና ስርዓትን በመከተል በዕውቀት ሪፎርሙን ማሳካት እንደሚገባ ተናግረው የህዝብን አመኔታ ከፍ ማድረግ እንደሚያስፈልግ አፈ ጉባኤዋ አሳስበዋል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ቦጋለ ፈይሳ በበኩላቸው ችግሮቻችንን በመለየት አሰራርን በቴክኖሎጂ በማዘመን ቀልጣፋ አሰራሮችን በፍርድ ቤቶች ለማስፈን ባለፉት ስድስት ወራት ውጤታማ ተግባራት መከናወናቸውን ገልጸዋል።
የፍትህ ስርዓቱ ላይ የሚታዩ ማነቆዎችን ለመፍታት በርካታ ተግባራት መከናወናቸውን ጠቁመው ተቋማት በአፈጻጸም ሂደት የሚታዩ ችግሮችን በመፍታት ቀጣይነት ያለው ለውጥ እንዲያስመዘግቡ መስራት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
የፍትህ ዘርፍ ትራንስፎርሜሽን ክልል አቀፍ ስትሪንግ ኮሚቴ ቅንጅታዊ አሰራር አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ ገልፀዋል።
በመድረኩ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አንዱዓለም አምባዬ የአፈጻጸም ሪፖርቱን ባቀረቡበት ወቅት ፍርድ ቤቶች የዜጎችን ሰብዓዊ መብትና የግለሰብ፣ የህዝብና የመንግስትን ኢኮኖሚያዊ መብቶች በማክበርና በማስከበር ረገድ ለአገር ዕድገትና ልማት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከቱ ይገኛል።
በፍትህ ዘርፍ ያሉ ጠንካራ ጎኖችን በማሳደግና ደካማ ጎኖችን በማረም የተገልጋይ እርካታን ማሳደግ እንደሚያስፈልግም አንስተዋል።
የክልሉ ፍትህ ቢሮ ምክትል ኃላፈ አቶ አድማሱ መንግስቱ በበኩላቸው የፍትህ ዘርፍ ትራንስፎርሜሽን ግቦችን ከማሳካት አንጻር የሚታዩ ክፍተቶችን በመለየት የመፍትሔ አቅጣጫ ላይ በትኩረት እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።
የመድረኩ ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያዬት በህዝቡ ዘንድ የሚነሳው የፍትህ አሰጣጥ ላይ ያለውን ጉድለት በማረም የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራት ከፍ ለማድረግ የድርሻቸውን እንደሚወጡ ተናግረዋል፡፡
ዘጋቢ፡ አይናለም ሰለሞን – ከሳውላ ጣቢያችን
More Stories
ቆሻሻን በአግባቡ በማስወገድ ከተማዋ ፅዱና ውብ እንድትሆን የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ ነው – የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች በቋሚነት የሚደገፉበት ስራ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የቡርጂ ዞን አስተዳደር አስታወቀ
“አንድ ሰው ወደዚህች ምድር ሲመጣ እንዲሰራ የተፈቀደለትና የሚጠበቅበት ነገር አለ” – ታደሰ ገብሬ /ጃክሰን/