አንትሮሽት ወይም የእናቶች ቀን በዓል በሃገርና በአለም አቀፍ ደረጃ ለማስተዋወቅና የቱሪዝም መዳረሻ ለማድረግ አየተሰራ መሆኑን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ገለጸ

አንትሮሽት ወይም የእናቶች ቀን በዓል በሃገርና በአለም አቀፍ ደረጃ ለማስተዋወቅና የቱሪዝም መዳረሻ ለማድረግ አየተሰራ መሆኑን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ገለጸ

ይህ የተገለጸው አንትሮሽት” ወይም የእናቶች የምስጋና አመታዊ ክብረ በዓል የማጠቃለያ መርሃ ግብር በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ ያሰሁራና ዋርቢያ ቀበሌ በድምቀት በተከበረበት ወቅት ነው።

“አንትሮሽት” ቃሉ ጉራጊኛ ሲሆን ትርጓሜውም የእናቶች የምስጋና ቀን ማለት ነው።

በመርሃ ግብሩ ላይ ተገኙት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ምክትል ሃላፊ አቶ ኑሪ ከድር አንትሮሽት ወይም የእናቶች የምስጋና ቀን በሃገርና በአለም አቀፍ ደረጃ ለማስተዋወቅና የቱሪዝም መዳረሻ ለማድረግ አየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

አንትሮሽት የሴቶች እኩልነት እንዲረጋገጥ እናቶች በልጆቻቸው አንዲያርፉ ከፍተኛ ሚና እንዳለውም አቶ ኑሪ ገልጸዋል።

የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ ባህል የአንድ ማህበረሰብ የማንነቱ መገለጫ እንደመሆኑ መጠን አንዳይበረዝና እንዳይጠፋ መጠበቅ ይገባል ብለዋል።

ጉራጌ ከሰለጠኑ የአለም ሃገራት አስቀድሞ የእናት ውለታን በመረዳት እናት መከበርና መመስገን አለባት በማለት አንትሮሽት ወይም የእናቶች የምስጋና ቀን በማለት ማክበር የጀመረ ማህበረሰብ መሆኑን አቶ ላጫ ተናግረዋል።

የጉራጌ ዞን ሴቶችና ህጻናት መምሪያ ሃላፊ ወይዘሮ ነጅሚያ መሃመድ በበኩላቸው የጉራጌ ብሄረሰብ ከጥንት ጀምሮ በወርሃ ጥር እየተከበሩ ካሉ ትልልቅ ሁነቶች መካከል አንትሮሽት የእናቶች ቀን በአል ተጠቃሽ ነው ብለዋል።

የእናቶችን ውለታ እና ሃላፊነት ማህበረሰቡ  ለእናሆቶች  ያለውን ፍቅርና ከበሬታን ለመግለጽ በአሉ እንደሚከበር ወይዘሮ ነጅሚያ ገልጸዋል።

በእዣ ወረዳ ያሰሁራና ዋርቢያ ቀበሌ አግኝተን ያነጋገርናቸው ተሳታፊ እናቶች  በሰጡት አስተያየት ከልጆቻችን ከብርና ምስጋ የምንቸርበት በልጆቻችን የምናርፍበት የደስታ በዓላችን ነው ሲሉ ገልጸዋል።

የ”አንትሮሽት” ወይም የእናቶች አመታዊ ክብረ በዓል በዞኑ በሚገኙ ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች  ሲከበር የነበረ ሲሆን በዛሬው ዕለት የማጠቃለያ መርሃ ግብሩ በማድረግ በቀጣይ የአንትሮሽት በዓል አበሽጌ ወረዳ የሚከበር መሆኑም ተገልጿል።

ዘጋቢ፡ አስቻለው አማረ-ከወልቂጤ ጣቢያችን