የኢፌዲሪ ስራና ክህሎት ሚኒስቴር ለማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ስራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ ከ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር በላይ የሚሆን ለቢሮ እና ለተለያየ አገልግሎት የሚውሉ ቁሳቁሶች ድጋፍ አደረገ
የተደረገው ድጋፍ ምቹ የስራ አካባቢን በመፍጠር በተቋሙ የተጀመረው የለውጥ ስራ ይበልጥ ውጤታማ እንዲሆን ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክትም የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ስራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ ገልጿል።
በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የተቋማዊ ለውጥ ስራዎች ስራ አስፈጻሚ አቶ በጋሻው ቅጣው በርክክቡ ወቅት እንዳሉት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከዚህ ቀደም ለሁሉም ክልሎች የማቴሪያል፣ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች እና ሌሎች ድጋፎችን ሲያደርግ ቆይቷል።
በተለይም ለማዕከላዊ ኢትዮጵያና ለደቡበ ኢትዮጵያ ክልሎች ከ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር በላይ የሚሆኑ ለቢሮ እና ለተለያየ አገልግሎት የሚውሉ ቁሳቁሶች ድጋፍ መደረጉን ገልፀዋል።
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በተለይም በሶስት ዋና ዋና ዘርፎች ማለትም በቴክኒክና ሙያ፣ በስራና ክህሎት እንዲሁም በአሰሪና ሰራተኛ ዘርፎች ላይ በትኩረት እንደሚሰራ አንስተዋል።
የተደረገው ድጋፍ ለሰራተኞች ምቹ የስራ አካባቢን በመፍጠር ለውጤታማነት እንዲተጉ እንደሚያስችል ተናግረው፤ መሠል ድጋፎች በቀጣይም ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ስራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ ሀላፊ አማካሪ አቶ እሸቱ ተሾመ በበኩላቸው፤ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉና ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው የተለያዩ ቁሳቁሶች ድጋፍ ማድረጉንና የተደረገው ድጋፍም ምቹ የስራ አካባቢን በመፍጠር በተቋሙ የተጀመረውን የለውጥ ጉዞ እንደሚያሳልጥ አመላክተዋል።
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ላደረገላቸው ድጋፍም አቶ እሸቱ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
በተቋሙ የተጀመሩ የለውጥ ስራዎች ይበልጥ ውጤታማ እንዲሆኑ መሠል ድጋፎች በቀጣይም ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው ጠቁመው፤ ለዚህ ውጤታማነትም ደግሞ ባለድርሻ አካላት አስፈላጊውን ድጋፍና ተሳትፎ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።
የቢሮው ሰራተኞች በሰጡት አስተያየትም የተደረገው ድጋፍ ከዚህ ቀደም ሲያጋጥማቸው የነበረውን የቁሳቁስ እጥረትን በመቅረፍና ለሰራተኞች ምቹ የሥራ አካባቢን በመፍጠር ከተቋማቸው የተሰጣቸውን ሃላፊነት በአግባቡ እንዲወጡ እንደሚያስችላቸው ገልፀዋል።
ዘጋቢ፡ መሐመድ ሽሁር – ከወልቂጤ ጣቢያችን
More Stories
ቆሻሻን በአግባቡ በማስወገድ ከተማዋ ፅዱና ውብ እንድትሆን የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ ነው – የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች በቋሚነት የሚደገፉበት ስራ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የቡርጂ ዞን አስተዳደር አስታወቀ
“አንድ ሰው ወደዚህች ምድር ሲመጣ እንዲሰራ የተፈቀደለትና የሚጠበቅበት ነገር አለ” – ታደሰ ገብሬ /ጃክሰን/