በጉራጌ ዞን ባለፋት ስድስት ወራት ለውጭ ገበያ ከቀረቡ ምርቶች ከ11 ሚሊየን ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱን የዞኑ ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ገለፀ

በጉራጌ ዞን ባለፋት ስድስት ወራት ለውጭ ገበያ ከቀረቡ ምርቶች ከ11 ሚሊየን ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱን የዞኑ ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ገለፀ

ይህ የተገለፀው መምሪያው የ2017 በጀት ዓመት የስድስት ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ግምገማና የ2ኛ ግማሽ በጀት ዓመት የዜጎች ቻርተር የውይይት መድረክ በወልቂጤ ከተማ ባካሄደበት ወቅት ነው።

መድረኩን በንግግር የከፈቱት የጉራጌ ዞን ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ሀላፊ አቶ መላኩ ብርሀኔ እንዳሉት፤ በጉራጌ ዞን ባለፋት ስድስት ወራት ለውጭ ገበያ ከቀረቡ ምርቶች ከ11 ሚሊየን ዶላር በላይ ገቢ ተገኝቷል።

በስድስት ወር ውስጥ የንግድ ምዝገባና ፈቃድ እድሳት ለማድረግ በተሰራዉ ስራ ከ11 ሺህ በላይ ነጋዴዎችን መመዝገብ መቻሉን ገልፀው፤ ከነዚህ ዉስጥ 8 ሺህ 8 መቶ ኦንላይን ማስገባት መቻሉም ተናግረዋል።

የመምሪያው ሀላፊ አክለውም የኑሮ ውድነቱን ለማረጋጋት ነባር የሸማች ማህበራትን በማጠናከርና አዳዲስ በማደራጀት ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል።

አቶ ነጋ አስፋው፣ በለጠ ሳሌና ኸይሪያ ጀማል የመድረኩ ተሳታፊዎች ሲሆኑ የሰንበት ገበያዎችን በማጠናከር የኑሮ ውድነቱን ለማረጋጋት ጥረት እያደረግን ነው ብለዋል።

በተጨማሪም ድጋፍ ለሚሹ የማህበረሰብ ክፍሎች የተለያዩ ድጋፍ ማድረጋቸውን ገልፀዋል።

ነባር ንግድ ፍቃድ በማሳደስ፣ አዲስ ንግድ ፍቃድ በኦንላይን በመስጠት ላይ መሆናቸውንም ተናግረዋል።

ዘጋቢ፡ አስፍር ሙህዲን – ከወልቂጤ ጣቢያችን