የሸኮ ብሔር የዘመን መለወጫ በዓል “ቲካሻ ቤንጊ”ን ማክበር ከሌሎች ህዝቦች ጋር ያለው የእርስ በእርስ ግንኙነትን ከማጠናከረም ባለፈ የብሔሩን ባህል፣ ወግ እና መልካም እሴቶችን ለዓለም ለማስተዋወቅ ያለው ፋይዳ ከፍተኛ መሆኑ ተገለጸ

የሸኮ ብሔር የዘመን መለወጫ በዓል “ቲካሻ ቤንጊ”ን ማክበር ከሌሎች ህዝቦች ጋር ያለው የእርስ በእርስ ግንኙነትን ከማጠናከረም ባለፈ የብሔሩን ባህል፣ ወግ እና መልካም እሴቶችን ለዓለም ለማስተዋወቅ ያለው ፋይዳ ከፍተኛ መሆኑ ተገለጸ

የሸኮ ብሔር የዘመን መለወጫ “ቲካሻ ቤንጊ” በዓል በቤንች ሸኮ ዞን በጉራፈርዳ ወረዳ በድምቀት ተከብሯል።

የሸኮ ብሄር ለዘመናት አብሮት የኖረ ባህል፣ ወግ እና የተለያዩ የባህል እሴት ባለቤት ነው።

ብሔሩ በየአመቱ ከጥር ወር መጀመሪያ አንስቶ እሰከ ጥር ወር መጨረሻ ምርቱን ሰብስቦ ወደ ጎተራ ካስገባ በኋላ ለዚህ ቀን በሰላም ያደረሰውን ፈጣሪ የሚያመሰግንበት በዓል ነው ቲካሻ ቤንጊ።

የሸኮ ብሔር የዘመን መለወጫ በዓል ቲካሻ ቤንጊ በጉራፈርዳ ወረዳ መከበሩ የሸኮ ህዝብ ከሌሎች ህዝቦች ጋር ያለው የእርስ በእርስ ግንኙነት ማጠናከሪያ ነው የሚሉት የቢፍቱ ከተማ አሰተዳደር ከንቲባ አቶ ኦሚስ ካሲከራ ናቸው።

የሸኮ ብሔር ዘመን መለወጫ ቲካሻ ቤንጊ ከመላው የሸኮና አካባቢው ህዝብ እንዲሁም ከአጎራባች ወረዳ፣ ዞን እና መላው የክልሉ ህዝብ ጋር በወንድማማችነት በተሻለ እና በደመቀ ሁኔታ በማክበር የሸኮን ህዝብ ባህል፣ ወግ እና መልካም እሴቶችን ለዓለም ለማስተዋወቅ ያለው ፋይዳ ከፍተኛ ነው ያሉት ደግሞ የጉራፈርዳ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታይጋይ ኤልያስ ናቸው።

ከበዓሉ ታዳሚዎች መካከል አንዳንዶች እንደተናገሩት የቲካሻ ቤንጊ በጉራፈርዳ ወረዳ መከበር የሸኮ ብሔር ከሌሎች ብሄረሰቦች ጋር ያለውን መቀራረብ የሚያሳይ እንደሆነ ገልፀው በቀጣይ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል።

በበዓሉ የጉራፈርዳ ወረዳ የሸኮ ብሄር የጎሳ መሪ እና የሜኤኒት ብሄረሰብ የጎሳ መሪዎች በዓሉ የሰላም እና የጤና እንዲሆን መርቀዋል።

በስነ-ሰርዓቱ ላይ የቤንች ሸኮ ዞን ሰላም እና ፀጥታ መምሪያ፣ የዞኑ ፖሊስ አዛዥን ጨምሮ ከፍተኛ አመራሮችና ጥሪ የተደረገላቸው ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

ዘጋቢ፡ ተመስገን ዳጉሳ – ከሚዛን ጣቢያችን