የማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎቶችን በማጠናከር የተሻላ የጤና ስርዓት መፍጠር እንደሚገባ ተገለፀ
ሪፍት ቫሊ ዩንቨርሲቲ ሆሳዕና ከምፓስ ከንግስት እሌኒ መሐመድ መታሰቢያ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ጋር በመተባበር የጽዳት ዘመቻና የደም ልገሳ መረሃ-ግብር በሆስፒታሉ ቅጥር ግቢ ውስጥ አካሂዷል።
በዋቸሞ ዩንቨርሲቲ የንግስት እሌኒ መሐመድ መታሰቢያ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ወርሃዊ የጽዳት ዘመቻና በየሦስት ወሩ ደግሞ የደም ልገሳ መርሃግብር እየተገበረ ይገኛል።
መርሃግብሩን የተቀላቀው ሪፍት ቫሊ ዩንቨርሲቲ ሆሳዕና ካምፓስ በዛሬው ዕለት ከሆስፒታሉ ሠራተኞች ጋር በመሆን በሆስፒታሉ ቅጥር ግቢ ውስጥ የጽዳት ዘመቻና የደም ልገሳ መረሃግብር አካሂዷል።
በመረሃግብሩ ላይ የተገኙት የሆስፒታሉ ዋና ስራ አስኪያጅ ዶ/ር ይድነቃቸው ደዳቸው የማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎቶችን በማጠናከር የተሻለ የጤና ስርዓት መፍጠር እንደሚገባ ተናግረዋል።
ሆስፒታሉ ተግባሩን ቀጣይነት ባለው መልኩ እንደሚያከናውን የተናገሩት ዶ/ር ይድነቃቸው ሪፍት ቫሊ ዩንቨርስቲ ሆሳዕና ካምፓስም በመረሃግሩ ላይ ያደረገውን ንቁ ተሳትፎ አድንቀው ሌሎችም ተቋማት ከካምፓሱ ልምድ በመውሰድ መሰል የማህበረሰብ አገልግሎቶች ላይ እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበዋል።
በመረሃግብሩ ላይ የተሳተፉት የሪፍት ቫሊ ዩንቨርስቲ ሆሳዕና ካምፓስ ዲን እጩ ዶክተር ነጋ አባቦራ ካምፓሱ ከመማር ማስተማርና ምርምር ስራዎች በተጨማሪ በማህበረሰብ አገልግሎት ዘርፍ ላይ በርካታ ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
የዛሬው መረሃግብር ለዚሁ አንዱ ማሳያ ነው ያሉት የካምፓሱ ዲን የማህረሰብ አገልግሎት ሕብረተሰቡንና አከባቢውን በተለያየ መልክ የሚያግዝ ከመሆኑም ባሻገር ለተማሪዎችም የተሻለ መስተጋብር ከአካባቢያቸው ጋር እንዲፈጥሩ የሚያስችል ነው ብዋል።
በዕለቱ በተከናወኑ በጽዳት ዘመቻና በደም ልገሳ መርሃግብር ላይ የተሳተፉ የካምፓሱና የሆስፒታሉ ሠራተኞች በየሙያ ዘርፋቸው ከሚሰጡት አግሎት ባሻገር በእንደዚህ አይነት መልካም ተግባራት ላይ መሳተፍ የአእምሮ እርካታን የሚፈጥር እንደሆነም አንስተዋል።
ዘጋቢ: አለቃል ደስታ -ከሆሳዕና ጣቢያችን

More Stories
የአፍላ ወጣቶችና ወጣቶችን የስነ ተዋልዶ ጤና ችግሮች ለመቅረፍ የተጀመሩ ጥረቶችን ለማጎልበት የጤና አደረጃጀቶችን ሚና ማሳደግ እንደሚገባ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ አስታወቀ
ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የመግባት ዕድል ያገኙ ተማሪዎች የበለጠ ውጤታማ ለመሆን ትምህርታቸው ላይ ብቻ ሊያተኩሩ እንደሚገባ መልዕክት ተላለፈ
የሀዲያ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ለ2018 በጀት ዓመት ከ10 ቢልዮን ብር በላይ በጀት ለተለያዩ የልማት ስራዎች እንዲውል በተገቢው እንደሚሠራ ገለፀ