የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ እንዳይሳካ ብዙ ጫናዎች ቢደረጉም ኢትዮጵያውያን በብሔራዊ ጉዳይ ስለማይደራደሩ በራስ አቅም የተጀመረውን የህዳሴ ግድብ ግንባታ ለማጠናቀቅ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርጉ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ትምህርት ቢሮ አመራሮችና ሰራተኞች ገለፁ።

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ እንዳይሳካ ብዙ ጫናዎች ቢደረጉም ኢትዮጵያውያን በብሔራዊ ጉዳይ ስለማይደራደሩ በራስ አቅም የተጀመረውን የህዳሴ ግድብ ግንባታ ለማጠናቀቅ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርጉ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ትምህርት ቢሮ አመራሮችና ሰራተኞች ገለፁ።

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ትምህርት ቢሮ አመራሮችና ሠራተኞች የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታን ለማጠናቀቅ የ155 ሺህ ብር የቦንድ ግዥ እንደሚፈፀም ተገልጿል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ትምህርት ቢሮ በቢሮ ሃላፊ ማዕረግ የክላስተሩ አማካሪና የቢሮው ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ተስፋዬ ደፋሩ፤ በራስ አቅም የተጀመረውን የታላቁ ህዳሴ ግድብን ለማጠናቀቅ ሀገራዊ ጥሪውን ተከትሎ ከቢሮው አመራሮችና ሠራተኞች የአንድ መቶ ሃምሳ አምስት ሺ ብር የቦንድ ግዥ ለመፈፀም ታቅዶ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

አክለውም ከቢሮው አመራሮችና ሰራተኞች ጋር በተደረገ ውይይት እንደየደመወዝ መጠናቸው ከ1 ሺ እስከ 5 ሺ ብር ድረስ ቦንድ እንደሚገዙ ገልፀው፤ እሳቸውም የ5000 ሺ ብር ቦንድ በመግዛት ተግባሩ የህልውና ጉዳይ ስለሆነ ሁሉም አሻራዉን እንዲያሳርፍ እስከ ታች ትምህርት ቤቶች ድረስ እንደሚወርድም ጠቅሰዋል፡፡

የቢሮው ምክትል ኃላፊና የአስተዳደርና ፋይናንስ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ታምሩ ቡራይና እንዲሁም የመምህራንና ትምህርት አመራር ልማት ዳይሬክቶሬት ቡድን መሪ አቶ ተስፋዬ ጫሬ በጋራ፤ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ እንዳይሳካ ከተለያየ አቅጣጫ ብዙ ጫናዎች ቢደረጉም ኢትዮጵያውያን በሀገር ጥቅም ጉዳይ ስለማይደራደሩ በራስ አቅም የተጀመረውን የህዳሴ ግድብ ግንባታ ለማጠናቀቅ ለ5ኛ ጊዜ ቦንድ መግዛታቸውን ገልጸው በቀጣይም አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል።

እንደ አቶ ታምሩ ቡራይና ገለፃ፤ ከዚህ ቀደም ለ4ኛ ጊዜ የፈፀሙትን የቦንድ ግዥ ገንዘብ ከመንግስት የተቀበሉ ቢሆንም ዛሬ ለ5ኛ ጊዜ የገዙት የ5000 ሺ ብር ቦንድ የማይመለስ ነው።

ወ/ሮ ባንቻየሁ ደበበ የአስተዳደርና ፋይናንስ ዘርፍ የኃላፊ ፀሐፊ ሲሆኑ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ከራሳቸው አልፎ ወደፊት ለልጆቻቸው የሚሸጋገር ሀብት በመሆኑ እንደ ከዚህ ቀደሙ ዛሬም የ1000 ብር ቦንድ በመግዛት አሻራቸውን ማሳረፋቸውን ተናግረዋል።

ዘጋቢ: በናወርቅ መንግሥቱ – ከጂንካ ጣቢያችን