ጀፎረ ዘመን የቀደመ ባህላዊ የምህንድስና ጥበብ አሻራ” በሚል መርህ የተዘጋጀ ዞናዊ የገጠር ኮሪደር ልማት ማስጀመሪያ መድረክ በጉራጌ ዞን እኖር ወረዳ ወሽዘውያር ቀበሌ በውቡ ኧሴዳሜ ጀፎረ ተካሄደ
“ጀፎረ ዘመንን የቀደመ ባህላዊ የምህንድስና ጥበብ አሻራ” በሚል መርህ የተዘጋጀ ዞናዊ የገጠር ኮሪደር ልማት ማስጀመሪያ መድረክ በጉራጌ ዞን እኖር ወረዳ ወሽዘውያር ቀበሌ በውቡ ኧሴዳሜ ጀፎረ ተካሄዷል ።
እንደ ሀገር የተጀመረው የገጠር ኮሪደር ልማት አጠናክሮ በማስቀጠል የጉራጌ ጀፎረን ማስተዋወቅ እና ለትውልድ ማስተላለፍ እንደሚያስፈልግ ተመላክቷል።
በመድረኩ ላይ የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ ፣ የዞኑ ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ አለማየሁ ገ/መስቀልን ጨምሮ የዞን፣ የወረዳና የከተማ አስተዳደር የስራ ኃላፊዎች፣ ከወልቂጤ ዩኒቨርስቲ፣ ከጉራጌ ልማትና ባህል ማህበር ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና የአካባቢው ነዋሪዎች ተገኝተዋል።
ዘጋቢ ፡ተረፈ ሀብቴ-ከወልቂጤ ጣቢያችን

More Stories
የፍርድ ቤቶች እና የፍትህ ሴክተር መስሪያ ቤቶች ጥምረት የፍትህ አሰጣጥ ላይ ውጤታማ ማድረጉ ተገለጸ
አቶ ዮሐንስ አበጋ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሀዲያ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሆነው ተሾሙ
የአፈር ጤናን በመጠበቅና ለምነትን በማሻሻል የአርሶ አደሮችን ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ምርምር ኢኒስቲትዩት የወራቤ ግብርና ምርምር ማዕከል አስታወቀ።