የጤና ሥራን ለማሳለጥ መረጃ ህይወት መሆኑን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ እንዳሻው ሽብሩ ተናገሩ
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ በክልሉ ላሉ ዞኖች አምቡላንሶች፣ ሞተር ብስክሌቶች፣ ኮምፒውተሮች እና ሌሎች ቁሳቁሶችን ድጋፍ አድርጓል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሰት ጤና ቢሮ ከኢፌዲሪ ጤና ሚኒስቴር ጋር በመቀናጀት ያገኛቸውን አምቡላንሶች፣ የሞተር ብስክሌቶች፣ ኮምፒውተሮች እና ሌሎች ቁሳቁሶችን ለክልሉ ዞኖች ድጋፍና ርክክብ ማድረጊያ መርሀ-ግብር አካሂዷል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ እንደሻው ሽብሩ፤ ክልሉ አዲስ እንደመሆኑ መጠን የተለያዩ በክልሉ ያሉ ዞኖች በርካታ የግብዓት እጥረት ያሉባቸው እንደመሆኑ አምቡላንስ፣ ሞተር ሳይክሎችና ኮምፒውተሮች ድጋፍ መደረጋቸውን አንስተዋል።
የጤናውን ሥራ ለማሳለጥ ብሎም ለጤና ሥራ መረጃ ወሳኝና ህይወት እንደመሆኑ ግብዓቶቹ ይህንን ችግር ከመፍታት አንፃር አይነተኛ ሚና እንደሚኖራቸው ተናግረዋል።
ከጤና ሚኒስቴር የተገኙትን 18 አምቡላንሶች፣ 20 ሞተር ሳይክሎችና 285 ኮምፒውተሮች ለሁሉም ዞኖች በፍትሐዊነት ድጋፍ የተደረገ መሆኑን ገልፀው ድጋፍ ያደረጉ አካላትን አመስግነዋል።
የተደረጉ ድጋፎች ለታለመላቸው አላማ እንዲውሉም አሳስበዋል።
የደቡብ ኦሞ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ ታምራት አሰፋ፣ የጋርዱላ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ ብርሃኑ ካኛልቤ እና የኣሪ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ ይሁን ጋሎ በጋር በሰጡት አሰተያየት፤ በድጋፉ መደሰታቸውን ገልጸው የጤና ልማት ሥራዎችን በተለይም ለእናቶችና ህፃናት ብሎም ለድንገተኛ አደጋዎች አገልግሎት ተደራሽነታችንን እንድናሰፋ የሚያስችለን ነው ብለዋል።
ዘጋቢ: ከተማ በየነ – ከጂንካ ጣቢያችን

More Stories
ህብር ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ የምርጫ ማኒፌስቶ፣ የዕጩ ማስተዋወቂያ እንዲሁም የምርጫ ቅስቀሳ ፕሮግራም በጎፋ ዞን ሳውላ ከተማ አካሄደ
ኦርቢስ ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ ጥራት ያለው የአይን ህክምና በሀገሪቱ ተደራሽ ለማድረግ በትኩረት እየሰራ መሆኑ ተገለፀ
ብልጽግና ፓርቲ የማህበረሰቡ ችግር የሚቀርፉ ፕሮጀክቶችን ገንብቶ በማጠናቀቅ በውጤታማነት ለአገልግሎት እያበቃ ነው – ዶ/ር መሀመድ ኑርዬ