1ኛው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት የታዳጊ ወጣቶች ስልጠና ፕሮግራም የምዘና ውድድር የመክፈቻ መርሀ-ግብር በሆሣዕና ከተማ በመካሄድ ላይ ይገኛል

1ኛው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት የታዳጊ ወጣቶች ስልጠና ፕሮግራም የምዘና ውድድር የመክፈቻ መርሀ-ግብር በሆሣዕና ከተማ በመካሄድ ላይ ይገኛል

በመክፈቻ ፕሮግራሙ ላይ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ አቶ ጌታቸው ሌሊሾ፣ የክልሉ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊና የስፖርት ዘርፍ ሀላፊ አቶ ሠይፈ ዓለሙን ጨምሮ ከክልልና ከዞን የተውጣጡ የመንግሥት የስራ ሀላፊዎችና የተለያዩ የስፖርት ፌደሬሽን ተወካዮች ተገኝተዋል።

የክልሉ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ አቶ ጌታቸው ሌሊሾ በመክፈቻ ንግግራቸው፤ ከምዘና ውድድሩ ለሀገር የሚተርፉ ምርጥ ስፖርተኞች የሚገኙበት በመሆኑ ሁሉም የሚመለከታቸው አካላት ውድድሩን በስፖርታዊ ጨዋነት እንዲያከናውኑ መልዕክት አስተላልፈዋል።

የክልሉ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊና የስፖርት ዘርፍ ሀላፊ አቶ ሰይፈ ዓለሙ በበኩላቸው፤ የታዳጊ ወጣቶች ምዘና ውድድሩ የክልሉን ስፖርት በአንድ ደረጃ ከፍ የሚያደርግና የሚያነቃቃ መሆኑን ገልፀዋል።

በምዘና ውድድሩ በስምንት የስፖርት አይነት ከዘጠኝ መዋቅር ከአንድ ሺ አምስት መቶ በላይ ልዑካን ይሣተፋሉ።

ዘጋቢ፡ ግዛቸው ደሳለኝ