ከኑሮ ውድነትና ከኢኮኖሚ ችግር ለመላቀቅ ያሉንን ፀጋዎች በአግባቡ በመጠቀም መስራት እንደሚያስፈልግ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ቢሮ ገለፀ
“ጠንካራና ሞዴል የሴቶች ልማት ህብረት አደረጃጀት በመፍጠር የሴቶችን ተጠቃሚነት እናረጋግጣለን” በሚል መሪ ቃል የንቅናቄ መድረክ በጎፋ ዞን ሣውላ ከተማ ተካሂዷል።
መንግስት የሴቶችን ሁለንተናዊ ብልጽግና ለማረጋገጥ እና በኢኮኖሚ፣ በማህበራዊና በፖለቲካ ዘርፍ ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆኑ በርካታ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ካሰች ኤልያስ ገልፀዋል።
ቀደም ሲል የሴቶች ልማት ቡድን ወደ ህብረት አደረጃጀት ከተቀየረ ወዲህ ከክልል ጀምሮ እስከ ቀበሌ መዋቅር ውጤታማ የሚያደርጉ ሥራዎች እየተሰሩ ይገኛሉ ያሉት ኃላፊዋ፤ የሴቶችና የህፃናትን መብትና ደህንነት ለማስጠበቅ በተሰሩ ተግባራት ለውጦች የተመዘገኑ ቢሆንም በቀጣይ የላቀ ሥራ የሚጠይቅ መሆኑን አስገንዝበዋል።
የሀገር ሁለንተናዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ ከልመና ወደ ምርታማነት እንሸጋገራለን በሚል የተቀመጠውን ራዕይ ለማሳካትና ከኑሮ ውድነት እና ከኢኮኖሚ ችግር ለመላቀቅ የሴቶች ሚና የላቀ በመሆኑ ያሉንን ፀጋዎች በአግባቡ ተጠቅመን መስራት እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል።
ለውይይቱ የተዘጋጀውን የንቅናቄ ሰነድ ያቀረቡት በሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ቢሮ የ(UNFPA) ፕሮግራም አስተባባሪና የሴቶች ተሳትፎ ንቅናቄ ማስፋፊያ ዳይሬክቶሬት ተወካይ አቶ ፈቀደ ፈለቀ፤ የኑሮ ውድነቱን ለማረጋጋት ሴቶች ትልቅ አቅም ያላቸው በመሆናቸው ያላቸውን ዕድልና አደረጃጀት በመጠቀም በመስራት ውጤታማ ሊሆኑ እንደሚችሉ አስገንዝበዋል።
የሴቶች ልማት ህብረት በበጎ ሥራዎች አቅመ ደካሞችና ወላጆቻቸውን ያጡ ህፃናት የመደገፍና የማገዝ፣ በደም እጦት የሚጎዱ ዜጎችን ህይወት ለመታደግ ደም በመለገስና በሴቶችና ህፃናት የሚፈፀሙ ጥቃቶችና ጎጂ ልማዳዊ ድረጊቶችን ለመከላከል ሚናቸው የጎላ መሆን እንዳለበት አመላክተዋል።
በመድረኩ የዞንና የወረዳ ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ኃላፊዎች፣ የተመረጡ ሞዴል የሴቶች ህብረት አደረጃጀት መሪዎችና የቀበሌ አስተዳዳሪዎች የተሳተፋ ሲሆን በሰጡት አስተያየትም ሴቶች በልማት ህብረት ተደራጅተው በመስራት ውጤት እያስመዘገቡ ስለመሆኑ ገልፀዋል።
ከተሳታፊዎች በተነሱ ሀሳቦች ከመድረክ ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቷል።
ዘጋቢ፡ አብርሃም ኩምሳ – ከሣውላ ጣቢያችን
More Stories
እርስ በርሳችን ከመቃቃር ይልቅ አንድነታችንን በሚያጠናክሩ ሀሳቦች ላይ ትኩረት በማድረግ ሁሉም የበኩሉን እንዲወጣ በጌዴኦ ዞን የይርጋጨፌ ከተማና ወረዳ አስተዳደር ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤቶች አሳሰቡ
የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታን ለማጠናቀቅ አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ እንደሚያደርጉ የጂንካ ዩኒቨርሲቲ ሠራተኞች ገለጹ
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከአንደኛዉ የብልጽግና ፓርቲ ድርጅታዊ ጉባኤ በኋላ በእርሻ ዘርፍ ግብርናዉን ለማዘመን በተደረገዉ ጥረት የሰብል ምርታማነት እያደገ መምጣቱ ተገለጸ