ስልጠናውን በንግግር የከፈቱት የኣሪ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብርሃም አታ የዜጎች ኑሮን ለማሻሻል በየአካባቢው ያሉ የተፈጥሮ ሀብቶችን በአግባቡ በመጠቀም በግብርናው ዘርፍ ዘላቂ ለውጥ ማምጣት ይጠበቅብናል ብለዋል።
በዚህ ሂደት በዘርፉ ሥራውን በቀጥታ የሚመሩ የግብርና ባለሙያዎች አርሶና አርብቶ አደር ማህብረሰቡ የአመራረትና የአረባብ ዘዴያቸውን በአዳዲስ አሠራሮች በመቀየር ሁሉ አቀፍ ለውጥ ለማስመዝገብ ተግተው መሥራት እንዳለባቸው አሳስበዋል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ቢሮ ኃላፊ በአቶ ኃ/ማርያም ተስፋዬ ስልጠናው በሀገር ደረጃ በግብርናው ዘርፍ ምርትና ምርታማነትን በእጥፍ በማሳደግ የግብርናውን ክፍለ ኢኮኖሚውን ፈጣን ሽግግር ለማድረግ ታስቦ እንደሆነ ተናግረዋል ።ዘርፉን ማዘመንና አዳዲስ አሠራሮችን ተግባራዊ ማድረግ ቁልፍ ተግባር ተደርጎ እየተሠራ እንዳለም ተብራርቷል ።
በ2023 ዓ/ም ከክልል አልፎ እንደ አገር ዘመናዊ ተክኖሎጂ መጠቀም ፣ህብረተሰቡን ከድህነት ማለቀቅ፣ በሀገሪቱ ለውጥና ብልጽግና ጉዞ ላይ በግብርናው ዘርፍ ሽግግር ማድረግ ግብ ተይዞ እየተሠራ እንዳለም ተገልጿል ።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊና የእንስሳት ጤናና ግብዓት አቅርቦት ኃላፊ ዶ/ር አዲሱ ኢዮብ ዜጎች ከተረጅነት ወደ ምርታማነት እንዲሸጋገሩ ፣የግብርና ባለሙያዎች እኩል የሥራ አቅም እንዲኖራቸውና በአጠቃላይ በግብርናው ዘርፍ የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ ታስቦ ስልጠናው መዘጋጀቱን አብራተዋል።
ዘጋቢ : ተመስገን አበራ-ከጂንካ ጣቢያችን
More Stories
ዲጂታል ኢትዮጵያን የመፍጠሪያ ጊዜን በማፋጠን ኢትዮጵያን የመጪው ዘመን መሪ ለማድረግ በትኩረት መስራት እንደሚገባ ተገለጸ
የሆሳዕና እናት ቃለ ህይወት ቤተክርስቲያን አዲሱን ዓመት ምክንያት በማድረግ ከአንድ መቶ በላይ ለሚሆኑ አቅመ ደካሞች የምግብ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገች
እመርታ ለዘላቂ ከፍታ!