ህዝበ ክርስቲያኑ የጥምቀት በዓልን ሲያከብር ወንድማማችነትና እህትማማችነትን በማጠናከር በአብሮነት መሆን አለበት – በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የጉራጌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ
ሀዋሳ፡ ጥር 11/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) ህዝበ ክርስቲያኑ የጥምቀት በዓልን ሲያከብር ወንድማማችነትና እህትማማችነትን በማጠናከር በአብሮነት መሆን እንዳለበት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የጉራጌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ ገለፁ፡፡
የጥምቀት በዓል በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ በተለያዩ ሃይማኖታዊ ስርዓቶች በድምቀት ተከብሯል፡፡
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የጉራጌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ በዚህ ወቅት እንደገለፁት የጥምቀት በዓል በእምነቱ ተከታዮች ዘንድ በየአመቱ በተለያዩ ሃይማኖታዊ ስርዓቶች በድምቀት የሚከበርና በዩኒስኮ የተመዘገበ ብሔራዊ የአዳባባይ በዓል ነው::
በመሆኑም ህዝበ ክርስቲያኑ በዓሉን ሲያከብር አቅመ ዳካሞችንና አረጋዊያን በመረዳት እንዲሁም ወንድማማችነትና እህትማማችነትን በማጠናከር በአብሮነት መሆን እንዳለበት ተናግረዋል፡፡
የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ በበኩላቸው በቤተ እምነቶችና በማህበረሰቡ መካከል ያለውን መልካም ግንኙነትና አንድነትን አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል ብለዋል፡፡
በተለይም ሰላም የሁሉም ነገሮች መሰረት በመሆኑ ለአካባቢያችንና ለሀገራችን ሰላም በጋራ መቆም እንደሚገባም አስገንዝበዋል፡፡
የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ዋና ከንቲባ አቶ ሙራድ ከዲር በዓሉ ሃይማኖታዊ ስርዓቱን በጠበቀ መልኩ በሰላምና በድምቀት እንዲከበር ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላደረጉ ባለድርሻ አካላትን አመስግነዋል፡፡
በከተማው የተጀመሩ የልማት ስራዎች ከዳር እንዲደርሱ ህብረተሰቡ እያደረገ ያለውን ድጋፍና ተሳትፎ አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በዓሉን በተለያዩ ሃይማኖታዊ ስርዓቶች በድምቀትና በሰላም ማክበር በመቻላቸው መደሰታቸውን የበዓሉ ታዳሚዎች ተናግረዋል፡፡
በዓሉ የመተሳሰብና የአብሮነት በዓል መሆኑንም ገልፀዋል፡፡
በበዓሉ ላይ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የጉራጌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ፣ የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ እንዲሁም የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ዋና ከንቲባ አቶ ሙራድ ከዲርን ጨምሮ ሌሎችም የዞኑና የከተማው የስራ ሃላፊዎችና የእምነቱ ተከታዮች ታድመዋል።
ዘጋቢ፣ ጅላሉ ፈድሉ – ከወልቂጤ ጣቢያችን
More Stories
በዲላ ከተማ የጥምቀት በዓል በሃይማኖታዊ ሥነ ስርዓት እየተከበረ ነው
በሀዲያና ስልጤ ሀገረ ስብከት በሆሳዕና ከተማ የጥምቀት ስርዓት እየተከናወነ ይገኛል
ፓርቲዉ ባለፉት 3 ዓመታት የብዝሃ ኢኮኖሚ መሪህ በመከተል እንደሀገር ዉጤታማ ተግባራትን ፈጽሟል-ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ