በዲላ ከተማ የጥምቀት በዓል በሃይማኖታዊ ሥነ ስርዓት እየተከበረ ነው

በዲላ ከተማ የጥምቀት በዓል በሃይማኖታዊ ሥነ ስርዓት እየተከበረ ነው

ሀዋሳ፡ ጥር 11/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) በዲላ ከተማ የጥምቀት በዓል በሃይማኖታዊ ሥነ ስርዓት እየተከበረ ነው፡፡

ይህንን የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን የጥምቀት በዓል ስናከብር ከክርስቶስ የተማርነውን ትህትና በመተግበር ሊሆን እንደሚገባ የጌዴኦ ኮሬ ቡርጂ ሃገረ ስብከት ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ብፁዕ አቡነ ገሪማ ተናግረዋል።

አክለውም በጥምቀቱ ባገኘነው በረከት መነሻ  ልጆቻችንን ከአልባለ ቦታ እንዳይውሉ በማስተማር  በኃይማኖት አንጸን ልናሳድጋቸው ይገባል ሲሉ ለህዝበ ክርስቲያኑ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

አሁን ላይ የጥምቀት ስርዓቱ ከተከናወነ በኃላ ባታ ለማሪያም፣ ልደታ ለማሪያም፣ ኢየሱስ  እና ሌሎች ታቦታት በታላቅ ኃይማኖታዊ ሥርዓት ወደ መንበራቸው እየተመለሱ ሲሆን ቀሪዎቹ ከዛሬ ጀምሮ ለሶስት ተከታታይ ቀናት እንደሚመለሱ ተገልጿል።

ዘጋቢ: እንግዳየሁ ቆሳ – ከይርጋጨፌ ጣቢያችን