በሀዲያና ስልጤ ሀገረ ስብከት በሆሳዕና ከተማ የጥምቀት ስርዓት እየተከናወነ ይገኛል
በዓሉ ኢየሱስ ክርስቶስ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ በመሄድ ፈጣሪ ሆኖ ሳለ በፍጡሩ ዮሐንስ እጅ በመጠመቅ ለሰው ልጆች ታላቅ ትህትናውን ያስተማረበት ታላቅ በዓል መሆኑን አባቶች በአስተምህሮታቸው ወቅት ገልፀዋል።
መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ኢየሱስ ክርስቶስን ባንተ መጠመቅ ሲገባኝ አንተን ላጠምቅ አይገባኝም ሲል ክርስቶስም “ጽድቅን ሁሉ መፈፀም ይገባናል” በማለት በሰው እጅ ሲጠመቅ ለሰው ልጆች ድህነት አርዓያ መሆኑን ያመላክታል ሲሉም ገልፀዋል።
የጥምቀት በዓል ክርስቶስ በልደቱ ሰማይን ምድርን እንዳስታረቀ ሁሉ በዛሬው የጥምቀት እለት ደግሞ በጥንተ ጠላት ዲያብሎስ በዮርዳኖስ ወንዝ የተቀበረን የእዳ ደብዳቤ በመቅደድ የሰው ልጆች ፍፁም ነፃነትን እንዲቀዳጅ ያደረገበት ቀን መሆኑን ጠቁመው በዓሉን መልካም ተግባራትን ሁሉ በመከወን ከአምላካችን በረከት የምናገኝበት ሊሆን ይገባል ሲሉም በትምህርታቸው አስገንዝበዋል።
ዘጋቢ: አማኑኤል አጤቦ – ከሆሳዕና ጣቢያችን

More Stories
ህዝበ ሙስሊሙ የመውሊድ በዓልን ሲያከብር በብዝሃነት ውስጥ የሚንፀባረቁ የመረዳዳትና የአብሮነት በጎ እሴቶችን ይበልጥ በማጠናከር ሊሆን እንደሚገባ ተገለጸ
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ኃላፊና የየዞን ከፍተኛ አመራሮች በሣውላ ማረሚያ ተቋም አረንጓዴ አሻራቸውን በማኖር ልዩ ልዩ የልማት ሥራዎችን ጎበኙ
በጌዴኦ ዞን ይርጋጨፌ ወረዳ የማህጸን በር ጫፍ ካንሰር ምርመራ እና ልየታ ተካሄደ