የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አብርሃም ቲርካሶ እንዳሉት፤ በክልሉ የከተራና የጥምቀት በዓላት በሰላማዊ ሁኔታ ተከብሮ እንዲጠናቀቅ በክልሉ በሚገኙ ሁሉም አካባቢዎች የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ተደርገዋል።
በክልሉ ጥር 10 ማለትም በከተራ በዓል 9 መቶ 24 ታቦታት ከመንበረ ክብራቸዉ ተነስተው ወደ ተዘጋጀላቸው ማረፊያ ስፍራ እንደሚንቀሳቀሱ ምክትል ኮሚሽነር አብርሃም ጠቅሰው፤ ታቦታቱ በሚያልፉባቸው መንገዶች ሁሉ እንቅስቃሴዎችን የሚያስተጓጉሉ ነገሮች እንዳይኖሩ ከሀይማኖት አባቶች፣ ከወጣቶችና ከማህበረሰቡ ጋር ሰፊ ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡
በክልሉ የከተራና የጥምቀት በዓላት ለተከታታይ 4 ቀናት በተለያዩ ሀይማኖታዊ ክዋኔዎች የሚከበሩ መሆናቸውን ጠቅሰዉ፤ በዓሉን ለማክበር ከሀገር ወስጥም ሆነ ከዉጭ የሚመጡ እንግዶች በሰላም እንዲመለሱ ለማድረግ ህብረተሰቡን ያሳተፈ አስተማማኝ የፀጥታ ስራ እየተሰራ ነዉ ብለዋል፡፡
የከተራና የጥምቀት በዓላት ላይ የስርቆትና ሌሎች ወንጀሎችም ሊከሰቱ ስለሚችሉ ምዕመኑ አስፈላጊዉን ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለበትም አሳበዋል፡፡
ህብረተሰቡ በዓሉን ለማክበር በሚያደረገው በማንኛውም እንቅስቃሴ ራሱን ከአደጋ በመጠበቅ ሊሆን እንደሚገባም ተናግረዋል።
ምዕመኑ በዓሉን በሚያከብርበት ወቅት ያልተገባ ድርጊት የሚፈጽሙትን ለፀጥታ አካላት ጥቆማ በመስጠት ትብብሩን እንዲያሳይም ጠይቀዋል።
ምክትል ኮሚሽነር አብርሃም በመጨረሻም ለመላው የእምነቱ ተከታዮች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ዘጋቢ: ተሻለ ከበደ – ከሆሳዕና ጣቢያችን

More Stories
የጉራጌ ዞን ትምህርት መምሪያ የ2018 ዓ.ም የክረምት ወራት የትምህርት ቅድመ ዝግጅት ስራዎች ግምገማ እና የ2019 ዓ.ም የተማሪዎች ቅበላ የንቅናቄ መድረክ እየተካሄደ ነው
የዳውሮ ዞን ምክር ቤት 4ኛ ዙር 13ኛ ሥራ ዘመን 29ኛ መደበኛ ጉባዔ መካሄድ ጀመረ
የህግ ታራሚዎችን አምራች ዜጋ ለማድረግ የስነ-ልቦና ድጋፍና የክህሎት ማጎልበቻ ስራዎች ወሳኝ መሆናቸው ተገለጸ