በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ዲላ ክላስተር የውኃ፣ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት የብልጽግና ፓርቲ መሠረታዊ የድርጅት አባላት ኮንፍራንስ እየተካሄደ ነው

ሀዋሳ፡ ጥር 09/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ዲላ ክላስተር የውኃ፣ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት የብልጽግና ፓርቲ መሠረታዊ የድርጅት አባላት ኮንፍራንስ እየተካሄደ ይገኛል።

‎ኮንፈረንሱ 2ኛው የብልጽግና ፓርቲ ጉባኤ ቅድመ ጉባኤ አካል መሆኑን በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የዲላ ክላስተር አስተባባሪ እና የውኃ ማዕድን እና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ እንዲሁም የመሰረታዊ ድርጅት አባል ኢንጅነር አክልሉ አዳኝ ተናግረዋል።

አክለውም በቀረበው ሰነድ በግልጽ የተቀመጡ አቅጣጫዎች መነሻ፤ በመጣንበት መንገድ በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚ፣ በማህበራዊ እና በዲፕሎማሲ ዘርፍ የተመዘገቡ ውጤቶች መኖራቸውን ጠቁመው፤ ውጤቶቹ የጋራ በመሆናቸው ማስፋት እንደሚገባ አሳስበዋል።

በመድረኩ የማዕከላዊ ኮሚቴ ሪፖርት፣ የህገ ደንብ ማሻሻያ፣ የመሰረታዊ ድርጅት የ6 ወር አፈጻጸም ሪፖርት እና ቀጣይ አቅጣጫ ማስቀመጥ፣ የኢንስፔክሽንና ስነ-ምግባር ኮሚሽን ሪፖርት እና የጉባኤ ተሳታፊዎች ምርጫ እንደሚከናወን በመርሃ ግብሩ ተመላክቷል።

‎በኮንፈረንሱ የክላስተሩ አመራሮችና የብልጽግና ፓርቲ መሠረታዊ ድርጅት አባላት እንዲሁም የመሰረታዊ ድርጅት ኢንስፔክሽንና ሥነ ምግባር ኮሚሽን አመራሮች ተሳታፊ ሆነዋል።

ዘጋቢ: እንግዳየሁ ቆሳ – ከይርጋጨፌ ጣቢያችን