አለም አቀፍ የዲፕሎማሲ ስራው ውጤታማ እንዲሆን ጠንካራ ጥረት ተደርጓል – አቶ ገ/መስቀል ጫላ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ም/ርዕሰ መስተዳድር
ሀዋሳ፡ ጥር 09/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) አለም አቀፍ የዲፕሎማሲ ስራው ውጤታማ እንዲሆን ጠንካራ ጥረት መደረጉን አቶ ገ/መስቀል ጫላ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ም/ርዕሰ መስተዳድር ገልፀዋል፡፡
“ከቃል እስከ ባህል” የብልፅግና ፓርቲ ቅድመ ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ የአርባ ምንጭ ክልል ማዕከል ኢኮኖሚ መሠረታዊ ድርጅት ኮንፍረንስ ተካሂዷል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ም/ርዕሰ መስተዳድር አቶ ገ/መስቀል ጫላ እንደተናገሩት ሀገሪቱን እየመራ የሚገኘው የብልፅግና ፓርቲ ለባለፉት በርካታ ጊዜያት የዲፕሎማሲ ስራዎችን ስኬት ጨምሮ የህዝቦችን ተጠቃሚነትን እያረጋገጠ መጥቷል።
ፓርቲው ለሁለተኛ መደበኛ ጉባኤን ከማካሄዱ አስቀድሞ በየደረጃው በአባላቱ ውይይት እያደረገ የተገኙ እምርታዎችን በመለየትና ያጋጠሙ ፈተናዎችን ለመቅረፍ በሚያስችል ደረጃ ስለመሆኑ ተናግረዋል።
ያለፉ ልምዶችን በመቀመር ያጋጠሙ ፈተናዎችን መሻገር ከመቼውም በላይ ይጠበቅብናል ያሉት ም/ርዕሰ-መስተዳድሩ በኮንፍረንሱ ማጠናቀቅያም ከአርባ ምንጭ ክልል ማዕከል ኢኮኖሚ ክላስተር የተወጣጡ አባላት በሀገር አቀፍ ደረጃ በሚካሄደው የፓርቲው ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ እንደሚሳተፉም አስታውቀዋል።
የአርባ ምንጭ ክልል ማዕከል ኢኮኖሚ መሠረታዊ ድርጅት ሰብሳቢ አቶ ሳሙኤል ሳድሁን በበኩላቸው የብልፅግና ፓርቲ ሀገሪቱ መንትያ መንገድ ላይ በነበረችበት ወቅት የተወለደ መሆኑን ተናግረው ሰፊውን የሀገሪቱን ህዝብ ብልፅግናን እያረጋገጠ ስለመምጣቱም አስታውሰዋል።
በመጨረሻም በቀረበው የፓርቲው ሪፖርት ቀርቦ መሠረታዊ ድርጅት አባላት ውይይት ያደረጉ ሲሆን በሀገር አቀፍ ደረጃ ከጥር 23 እስከ 25 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ በሚካሄደው ጉባኤ ላይ የሚሳተፉ አባላትም ምርጫ ተካሂዷል።
ዘጋቢ፡ በኃይሉ ሙሉጌታ – ከአርባምንጭ ጣቢያችን
More Stories
ቆሻሻን በአግባቡ በማስወገድ ከተማዋ ፅዱና ውብ እንድትሆን የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ ነው – የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች በቋሚነት የሚደገፉበት ስራ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የቡርጂ ዞን አስተዳደር አስታወቀ
“አንድ ሰው ወደዚህች ምድር ሲመጣ እንዲሰራ የተፈቀደለትና የሚጠበቅበት ነገር አለ” – ታደሰ ገብሬ /ጃክሰን/