የብልጽግና ፓርቲ 1ኛ መደበኛ ጉባኤ ያስቀመጣቸዉ አቅጣጫዎችና ባስተላለፋቸዉ ዉሳኔዎች መሰረት በርካታ ስኬቶች መመዝገባቸዉ ተገለጸ
የብልጽግና ፓርቲ 1ኛ መደበኛ ጉባኤ ያስቀመጣቸዉ አቅጣጫዎችና ባስተላለፋቸዉ ዉሳኔዎች መሰረት በርካታ ስኬቶች መመዝገባቸዉን የፓርቲዉ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባልና በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ኡስማን ሱሩር ገለፁ።
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ዱራሜ ክላስተር “ ከቃል እስከ ባህል” በሚል መሪ ቃል የብልጽግና ፓርቲ አባላት ኮንፈረንስ ተካሂዷል።
ከፓርቲዉ 1ኛ መደበኛ ጉባኤ ወዲህ በግብርና ዘርፍ ከተረጅነት ለመላቀቅ በስንዴ ምርት ራስን ከመቻል አልፎ እስከ ኤክስፖርት ድረስ ዉጤታማ ስራ መከናወኑን የገለፁት የፓርቲዉ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባልና በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ኡስማን ሱሩር፣ በሌማት ትሩፋትና በአረንጓዴ ልማት ስራዎችም ዉጤት መታየቱን ገልፀዋል። ይሄዉ ተግባር ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም ተናግረዋል።
ኮንፈረሱም ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ መመሪያዎችን ከማጽደቅ ጀምሮ የፓርቲዉ 2ኛ መደበኛ ጉባኤ ተሳታፊዎችን መምረጡን ጠቅሰዋል።
በፓርቲዉ መሪነትና በመንግስት ፈፃሚነት ባለፉት የለዉጥ ዓመታት የህብረተሰቡን ህይወት የሚቀይሩ በርካታ ተግባራት መከናወናቸዉን የጠቀሱት የመድረኩ ተሳታፊ የሆኑት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ደንና አከባቢ ጥበቃ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ አብረሃም መጫ እና የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጌታቸዉ ለሊሾ፣ በክላስተሩ የሚገኙ ተቋማት የተሳሰሩና ለጋራ ስኬት የሚሰሩ ናቸዉ ብለዋል።
በመድረኩ በ2ኛዉ የብልጽግና ፓርቲ መደበኛ ጉባኤ ላይ የሚሳተፉ አባላትም ተመርጠዋል።
ዘጋቢ: ድልነሳው ታደሰ
More Stories
ቆሻሻን በአግባቡ በማስወገድ ከተማዋ ፅዱና ውብ እንድትሆን የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ ነው – የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች በቋሚነት የሚደገፉበት ስራ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የቡርጂ ዞን አስተዳደር አስታወቀ
“አንድ ሰው ወደዚህች ምድር ሲመጣ እንዲሰራ የተፈቀደለትና የሚጠበቅበት ነገር አለ” – ታደሰ ገብሬ /ጃክሰን/