በህብረ ብሔራዊ አንድነት የብልጽግና ፓርቲ ጉዞ እውን እንዲሆን የፓርቲው አባላት ግንባር ቀደም ሚናቸውን መወጣት እንዳለባቸው ተገለፀ
“ከቃል እስከ ባህል” የጂንካ ክላስተር ማህበራዊ ዘርፍ ብልጽግና ህብረት የሁለተኛው ብልጽግና ፓርቲ ጠቅላላ ጉባኤ የቅድመ ጉባኤ አባላት ኮንፈረንስ በጂንካ ከተማ ተካሂዷል።
በመድረኩ በመገኘት መልዕክት ያስተላለፉት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ ማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪ እና የክልሉ ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር አበባየሁ ታደሰ እንደገለፁት፤ ብልጽግና ፓርቲ በሀገር ደረጃ ፖለቲካ ምህዳሩ እንዲሰፋ ትልቅ ዕድል ይዞ መጥቷል።
የፓርቲው አባላት በሁሉም የልማት ዘርፎች ግንባር ቀደም ሚናቸውን በመወጣት ለህዝቡ ተጠቃሚነት ሊሠሩ እንደሚገባም ዶ/ር አበባየሁ አሳስበው፤ በየአካባቢው ያሉ ፀጋዎችን በተገቢው በመለየት መጠቀም ያስፈልጋል ብለዋል።
በክልሉ ስር በርካታ ብሔር ብሔረሰቦች የሚገኙ ሲሆን ይህ ደግሞ ለተሻለ አንድነትና የልማት አቅም የሚፈጥር ነው ሲሉም ገልፀዋል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊና የማህበራዊ ክላስተር ብልጽግና ፓርቲ መሠረታዊ ድርጅት ሰብሳቢ አቶ ኢሳይያስ እንዲሪያስ፤ ፓርቲው በወንድማማችነትና እህትማማችነት መንፈስ በመተጋገዝና በመተባበር ከጊዜ ወደ ጊዜ አመርቂ ውጤት እንዲመዘገብ አድርጓል ብለዋል።
ሁሉም በሚሠራበት መሥሪያ ቤት ተግቶ በመሥራት በውጤታማነትና በተግባር አፈፃፀም ግንባር ቀደም ሚና መጫወት ይገባል ሲሉም መልዕክት አስተላልፈዋል።
የኮንፈረንሱ መድረክ ዋና ዓላማ ከፊታችን የሚካሄደው የብልጽግና ፓርቲ ጉባኤ ስኬታማ እንዲሆን ለማስቻልና በጉባኤው ተሳተፊዎችን ለመለየት ነው ብለዋል አቶ ኢሳይያስ።
በመድረኩ ከዚህ በፊት በፓርቲው የተከናወኑ ተግባራት በዝርዝር ቀርበው ገንቢ አስተያየትና ውይይት ተደርጎበታል።
የመድረኩ ተሳታፊ የፓርቲው አመራርና አባላት በፓርቲው በኩል የሚተላለፉ ውሳኔዎችንና እሳቤዎችን ወደ ተግባር ለመቀየር እንደሚሠሩ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
የብልጽግና ተምሳሌትና የተሻለች ኢትዮጵያን ለማየት በየሥራ መስካቸው ሙያዊ ሀላፊነታቸውን ከመቸውም ጊዜ በላይ ለመወጣት እንደሚሠሩም ገልፀዋል።
ዘጋቢ: ተመስገን አበራ – ከጂንካ ጣቢያችን
More Stories
የቀን 6፡00 ዜና 24፤ ሀዋሳ፡ ጥር 13/2017 ዓ.ም
የማታ 1፡00 ዜና 24፤ሀዋሳ፡ ታህሳስ 29/2017 ዓ.ም
የገናና ጥምቀት በዓላትን ምክንያት በማድረግ የህዝብ ፍሰት ከወትሮው የሚጨምር በመሆኑ ህብረተሰቡ ቀልጣፋ የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲያገኝ የተቀናጀ ስራ እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ