የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የጌዴኦ አግሮፎረስትሪ ተጠብቆ እንዲቆይ የድርሻዋን እየተወጣች ነው ሲል የጌዴኦ ዞን አስተዳደር ገልጿል።
ዙሪያዋን በሀገር በቀል ዛፎች የተከበበችው የሀንዲዳ መድኃኒዓለም ቤተክርስቲያን ከዲላ ከተማ በ7 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ትገኛለች።
የቤተክርስቲያኗ አስተዳዳሪ መላከሰላም ቀሲስ ጥላሁን ተሰማ ከ40 ዓመት በፊት 4 ሺህ የዛፍ ችግኞችን በማምጣት መትከላቸውን ተናግረዋል።
ቤተክርስቲያኗ ያላት ቅርስም ሆነ ትልቁ ውበቷ ደን ነው ያሉት አቶ መኮንን ሰይፉ፤ ለአየር ንብረት ለውጥ መፍትሔ ከማበጀት ባለፈ የቱሪዝም መዳረሻ ለማድረግ እየተሰራ እንዳለ ጠቁመዋል።
ትውልድን በስነ-ምግባር ለማነጽ ከዚህ ቀደም ሰሜን ላይ ብቻ የነበረው የአብነት ትምህርት ቤት ለመገንባት ከ60 ሚሊየን ብር በላይ በሀገረ ስብከቱ ተመድቦ እንቅስቃሴ መጀመሩም ተገልጿል።
የሀንዲዳ ደብረሰላም መድሐኒዓለም ቤተክርስቲያን በአካባቢ ጥበቃና የተፈጥሮ ሀብት አያያዝ የበኩሏን እየተወጣች ነው ያሉት የጌዴኦ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዶክተር ዝናቡ ወልዴ፤ በUNESCO ለተመዘገበው አግሮፎረስትሪ በቤተክርስቲያኗ የሚገኙ የረዥም ዘመን ጥብቅ ደኖች ትልቅ አበርክቶ እንዳላቸው ተናግረዋል።
ቤተክርስቲያኗ ከተፈጥሮ ጥበቃ ባለፈ በትምህርቱ ዘርፍ እየሰራች ያለችውን ስራ ዶ/ር ዝናቡ አድንቀዋል።
ዘጋቢ፡ ውብሸት ካሣሁን – ከይርጋጨፌ ጣቢያችን

More Stories
የፍርድ ቤቶች እና የፍትህ ሴክተር መስሪያ ቤቶች ጥምረት የፍትህ አሰጣጥ ላይ ውጤታማ ማድረጉ ተገለጸ
አቶ ዮሐንስ አበጋ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሀዲያ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሆነው ተሾሙ
የአፈር ጤናን በመጠበቅና ለምነትን በማሻሻል የአርሶ አደሮችን ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ምርምር ኢኒስቲትዩት የወራቤ ግብርና ምርምር ማዕከል አስታወቀ።