ለህዳሴ ግድብ ቦንድ በመግዛት ለቀጣይ ትውልድ አሻራቸውን በማስቀመጣቸው ደስተኛ መሆናቸውን የዲላ ዙሪያ ወረዳ ነዋሪዎች ተናገሩ
የወረዳው አስተዳደር በበኩሉ ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ቦንድ በመግዛት የበኩላቸውን ለተወጡ አካላት ምስጋና አቅርቧል።
የታላቁ የህዳሴ ግድብ ዋንጫ ታህሳስ 16 ቀን 2017 ዓ.ም በጌዴኦ ዞን ዲላ ከተማ መግባቱን ተከትሎ በዞኑ በተለያዩ መዋቅሮች ገቢ የማሰባሰብ ሥራ እየተከናወነ ይገኛል።
በዚህም በያዝነው ጥር 01/2017 ዓ.ም ዋንጫውን በዞኑ የዲላ ዙሪያ ወረዳ ከረጴ ወረዳ አቀባበል ማድረጉን ተከትሎ የቦንድ ግዥ እየተከናወነ ይገኛል።
የቦንድ ግዥ ሲያከናውኑ ካገኘናቸው የወረዳው ነዋሪዎች መካከል ወ/ሮ ውድነሽ ገመቹ እና አቶ ግዛቸው ታደሰ በወረዳው የሽገዶ እና ሚችለ ግሪሳ ቀበሌ ነዋሪዎች ሲሆኑ የህዳሴ ግድብ ለታሪክ አሻራ የምናስቀምጥበት በመሆኑ የግድቡ ግንባታ ሥራ እስኪጠናቀቅ አስፈጊውን ድጋፍ እናደርጋለን ብለዋል።
አቶ ግዛቸው ዘውዴ እና አቶ አለማየሁ ብሬ በወረዳው ከአንዲዳ እና አይጥለ ሱኬ ቀበሌ ቦንድ የገዙ የወረዳው ነዋሪዎች ሲሆኑ የቦንድ ግዥ የቁጠባ ባህላችንን ከማሳደግ ባሻገር የሃገራችንን ብልጽግና ለማረጋገጥ እየተገነባ ያለ ትልቅ ፕሮጀክት በመሆኑ ይህንን ዕድል በማግኘታቸው ደስታ እንደተሰማቸው ነው የተናገሩት።
የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታሪኩ ታደሰ በበኩላቸው፤ የህዳሴ ግድብ የሀገራችን ህዝቦች ያስተሳሰረ እና አንድነታችንን ለዓለም ያሳየንበት መሆኑን በመግለጽ የቦንድ ግዥ ያከናውኑ አካላትን አመስግነዋል።
አስተዳሪው አክለውም የወረዳው ባለሃብቶች፣ አመራሮች፣ ነጋዴ ማህበረሰብ እና ሁሉም የወረዳው ነዋሪዎች የህዳሴ ግድብ ቦንድ በመግዛት የበኩላቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል።
ዘጋቢ: እንግዳየሁ ቆሳ – ከይርጋጨፌ ጣቢያችን
More Stories
ለዜጎች ሰላምና ለሀገር ዕድገት የጸጥታዉ ዘርፍ ያለው ሚና ከፍተኛ መሆኑ ተገለጸ
የተገልጋይ እርካታን ለማሳደግ ፈጣንና ቀልጣፉ አገልግሎት በመስጠት የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎችን ከግብ ማድረስ እንደሚገባ ተገለጸ
በሁሉም የትምህርት ስራዎች የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ ባለድርሻ አካላት በቁርጠኝነት ሊንቀሳቀሱ ይገባል ሲል የቤንች ሸኮ ዞን አስተዳደር አሳሰበ