በብሔሩ ዘንድ በጥር ወር የሚከበረው የ2017 ዓ.ም የዘመን መለወጫ ዳራሮ በዓል የጌዴኦ ህዝብ የባህል አስተዳዳሪ መሪ አባ ጋዳ ቢፎሚ ዋቆ ቤት ተከብሯል፡፡
ዛሬ በብሄሩ ዘንድ ጥር 1 የአዲስ ዓመት መግቢያ በዓል በመሆን ነው የተከበረው።
የ2017 ዓ.ም የዘመን መለወጫ ዳራሮ በዓል በዲላ ዙሪያ ወረዳ ወቸማ ሆጢቻ በሚገኘው ፋዬሞ ሶንጎ በሁሉቃ፣ በፋጎና በተለያዩ ኩነቶች መከበር ጀምሯል።
ዳራሮ የጌዴኦ ህዝብ የአዲስ ዓመት ማብሰሪያና የአዲስ ዓመት ተስፋ መሰነቂያ የዕርቅና የይቅርታ በዓል ነው።
በዓሉ የሚከበረው ከአሮጌው ዓመት ወደ አዲስ ዓመት ያሸጋገረው ፈጣሪ የሚመሰገንበት ከጥንት አባቶቻችን የመጣውን አኩሪ ባህል ለቀጣይ ትውልድ በማስተማር ለማሸጋገር ዓላማ ያደረገ ነው።
በብሔሩ ዘንድ በጥር ወር የሚከበረው የ2017 ዓ.ም የዘመን መለወጫ ዳራሮ በዓል የጌዴኦ ህዝብ የባህል አስተዳዳሪ መሪ አባ ጋዳ ቢፎሚ ዋቆ ቤት ተከብሯል፡፡
የዘንድሮው ዳራሮ በዓል በአባ ጋዳ፣ በአባ ሮጋዎች፣ በሁላቲ ሃይቻዎች እና በዎዮዎች ቤት በየደረጃ እየተከበረ ይገኛል።
በበዓሉ በሀገሪቱ ያሉ የተለያዩ ሰው ሰራሽና የተፈጥሮ አደጋዎች እንዲጠፉ ጸሎትና ልመና ተደርጓል።
ይህንን ለፈጣሪ ልመናና ምስጋና የሚቀርብበት በዓል ለትውልድ ለማሸጋገር እና ጠብቆ ለማቆየት እየተሰራ እንዳለም ተገልጿል።
ዳራሮ በዓል በየዓመቱ በጥር ወር ውስጥ ከአንጋፋው ኦዳ ያአ ሶንጎ መከበር የሚጀመር ሲሆን በሁሉም ወረዳዎች በሚገኙት አንጋፋ ሶንጎች እየተከበረ ቆይቶ ማጠቃለያ በዞን ደረጃ በዲላ ስታዲየም በድምቀት በተለያዩ ዝግጅቶች ይከበራል።
የዘንድሮው ዳራሮ በዓል በቡሌ ወረዳ በሚገኘው አንጋፋው ኦዳ ያአ ሶንጎ ጥር 03/2017 ዓ.ም መከበር እንደሚጀመር ተገልጿል።
ዘጋቢ፡ ውብሸት ካሣሁን – ከይርጋጨፌ ጣቢያችን

More Stories
ህብር ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ የምርጫ ማኒፌስቶ፣ የዕጩ ማስተዋወቂያ እንዲሁም የምርጫ ቅስቀሳ ፕሮግራም በጎፋ ዞን ሳውላ ከተማ አካሄደ
ኦርቢስ ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ ጥራት ያለው የአይን ህክምና በሀገሪቱ ተደራሽ ለማድረግ በትኩረት እየሰራ መሆኑ ተገለፀ
ብልጽግና ፓርቲ የማህበረሰቡ ችግር የሚቀርፉ ፕሮጀክቶችን ገንብቶ በማጠናቀቅ በውጤታማነት ለአገልግሎት እያበቃ ነው – ዶ/ር መሀመድ ኑርዬ