በሥራ ዕድል ፈጠራ የተደራጁ ወጣቶች ከተጠቃሚነታቸው ባለፈ በፈጠራ ስራቸው ለማህበረሰቡ ችግር ፈቺ አገልግሎቶችን እየሰጡ እንደሆነ በዳውሮ ዞን የገና ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪ ገልፀዋል።
በወረዳው ለመፀዳጃ ቤት አገልግሎት የሚውል ቁሳቁስ ለማምረት የተደራጁ ወጣቶች በተሰማሩበት የሥራ መስክ የክህሎት ስልጠና ተሰጥቷል።
እንደ ሀገር የተጀመረውን ጽዱ ኢትዮጵያ ንቅናቄ አካል የሆነውን የመፀዳጃ ቤት አገልግሎትን ለማሳለጥ የሚያስችል ስልጠና ስለመሆኑም ተገልጿል፡፡
በመርሃ ግብሩ የተገኙት የገና ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ቡላዶ ቡልቱሞ በዚሁ ወቅት እንደገለፁት፤ ወጣቶች ከስራ ጠባቂነት ተላቀው ለማህበረሰቡ ችግር ፈቺ የሆኑ የፈጠራ ስራዎችን በመስራት ተጠቃሚ ሆነዋል።
እነዚህንና ተመሳሳይ ስራዎችን ወጣቶች ተደራጅተው በመስራት ለሌሎችም ተምሳሌት መሆን እንዳለባቸው ጠቁመዋል።
በተጨማሪም ወጣቶች ያመረቱትን ለመፀዳጃ ቤት አገልግሎት የሚውሉትን ምርቶች ህብረተሰቡ ገዝቶ ተጠቃሚ መሆን እንዳለበትም አሳስበዋል።
የወረዳው ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ዘነበ ዳማ በበኩላቸው፤ የዚህ ቁስ ማምረት ዋና ዓላማው እንደ ሀገር የተጀመረውን ጽዱ ኢትዮጵያ ንቅናቄ አካል የሆነውን የመፀዳጃ ቤት አገልግሎትን ለማሳለጥ መሆኑንም ተናግረዋል።
ይህም ለወጣቶች የስራ ዕድል ከመፍጠር አልፎ ለአካባቢውም ህብረተሰብ ልዩ ጥቅም እንደሚሰጥ አክለው ገልፀዋል።
በስልጠናው ከተሳተፉት መካከል ወጣት ሳሙኤል ጋሻው፣ ሻዋን ሳላጦ እና አብርሃም ወጁ በሰጡት አስተያየት፤ የተመቻቸላቸው የስልጠና መርሃ ግብር ግንዛቤ ከመፍጠሩ ባለፈ የማህበረሰቡን ችግር ፈቺ የሆኑ ስራዎች ላይ ለመሰማራት ዕድል እንደፈጠረላቸው ተናግረዋል።
ወጣቶቹ በስልጠና ወቅት ያገኙትን እውቀትና ክህሎት ተጠቅመው ለሌሎች ስራ አጥ ወጣቶችም የስራ ዕድል በማመቻቸት በኩል ህብረተሰቡን የሚጠቅሙ ስራዎችን እንደሚያጠናክሩ አንስተዋል።
የመስሪያ እና ማምረቻ ቦታ በማመቻቸት እንዲሁም የገበያ ትስስርን ከመፍጠር አኳያ ትብብር እንዲያደርጉላቸውም ጠይቀዋል።
ስልጠናው ለአራት ተከታታይ ቀናት በክልሉ በተመረጡ ወረዳዎች በዘርፉ ለተደራጁ ወጣቶች መሰጠቱም ተመላክቷል።
ዘጋቢ፡ አፈወርቅ ኦሹ – ከዋካ ጣቢያችን
More Stories
የዘንድሮው የጌዴኦ ብሔር የዘመን መለወጫ ዳራሮ በዓል በተለያዩ ኩነቶች መከበር ጀመረ
በእንስሳት እርባታና በጓሮ አትክልት ሥራ በመሰማራታቸው ውጤታማ መሆናቸውን በወላይታ ዞን የአረካ ከተማ አንዳንድ ነዋሪዎች ገለጹ
በክልሉ ከሚገኙ ሁሉም ተቋማት ጋር የመረጃ ግንኙነት በማጠናከር በሁሉም ዘርፎች የህብረተሰቡን ፍትሀዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት እየተሰራ ነው – የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፕላንና ልማት ቢሮ