ሀዋሳ፡ ታህሳስ 30/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) በክልሉ ከሚገኙ ሁሉም ተቋማት ጋር የመረጃ ግንኙነት በማጠናከር በሁሉም ዘርፎች የህብረተሰቡን ፍትሀዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት እየሰራ መሆኑን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፕላንና ልማት ቢሮ ገለፀ።
ከተሞች መዘመን እንዲችሉ በከተሞች የሚገነቡ ግንባታዎች ደረጃቸውን የጠበቁ እንዲሆኑና የኮሪደር ልማቶችን ጥራት ለማስጠበቅ ተገቢ ክትትል እየተደረገ መሆኑም ተገልጿል::
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፕላንና ልማት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ባዩሽ ተስፋዬ፤ የክልሉ መንግስት ለሰላም መስፈን በሰጠው ልዩ ትኩረት የተገኘውን አስተማማኝ ሰላም በሁሉም የልማት ዘርፎች ለመድገም የጠራ መረጃ ማሰባሰብና ማሰራጨት ላይ ትኩረት ተደርጎ እየተሰራ ነው ብለዋል።
ጥራት ያለውን ትምህርትን፣ መከላከልን መሰረተ ያደረገ የጤና ሽፋን በማሳደግ፣ በምግብ ዋስትና፣ በመሰረተ ልማት አውታሮችና በሌሎች የልማት ፕሮጀክቶች ህብረተሰቡን ውጤታማና ፍትሃዊ ተጠቃሚ ለማድረግ ትክክለኛ መረጃን ማሰባሰብ እና ማሰራጨት የሚችል የመረጃ ዌብ ሳይት በማበልጸግ እየተሰራ ነው ብለዋል።
በክልሉ ከሚገኙ ሁሉም ተቋማት ጋር የመረጃ ግንኙነት በማጠናከር በሁሉም ዘርፎች የህብረተሰቡን ፍትሐዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት እየሰራ መሆኑንም ዶክተር ባዩሽ አመላክተዋል::
ከኢኮኖሚ ዕድገት የተመጣጠነ፣ አምራች እና የበለጸገ ህብረተሰብ ለመፍጠር በስነ-ህዝብ ምጣኔ ላይ ልዩ ትኩረት መደረጉንም ዶክተር ባዩሽ ጠቁመዋል።
ከ2016 ዓ.ም ጀምሮ የኑሮ ውድነትን ለመከላከልና ገበያን ለማረጋጋት በተሰራው ስራ በክልሉ 104 የሰንበት ገበያ በማቋቋም አበረታች ለውጥ ተመዝግቧል ብለዋል።
ክልሉ የብዝሃ ማዕከላት በመሆኑ የሚገነቡ ግንባታዎች ደረጃቸውን የጠበቁ እንዲሆኑ የኮሪደር ልማቶች ጥራታቸውን ለማስጠበቅ ተገቢ ክትትል እየተደረገ መሆኑንም ዶክተር ባዩሽ ገልጸዋል።
ዘጋቢ: ሳሙኤል መንታሞ – ከሆሳዕና ጣቢያችን
More Stories
የዘንድሮው የጌዴኦ ብሔር የዘመን መለወጫ ዳራሮ በዓል በተለያዩ ኩነቶች መከበር ጀመረ
በእንስሳት እርባታና በጓሮ አትክልት ሥራ በመሰማራታቸው ውጤታማ መሆናቸውን በወላይታ ዞን የአረካ ከተማ አንዳንድ ነዋሪዎች ገለጹ
በሥራ ዕድል ፈጠራ የተደራጁ ወጣቶች ከተጠቃሚነታቸው ባለፈ በፈጠራ ስራቸው ለማህበረሰቡ ችግር ፈቺ አገልግሎቶችን እየሰጡ እንደሆነ ተገለጸ