የወልቂጤ ከተማ የወንጌላዊያን አብያተ ክርስቲያናት ወጣቶች ህብረት ከወልቂጤ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ጋር በመተባበር የገናን በዓልን ምክንያት በማድረግ ለአቅመ ደካማ የህብረተሰብ ክፍሎች ድጋፍ አደረገ
የወልቂጤ ከተማ ከንቲባ አቶ ሙራድ ከድር የገና በዓል ፍቅር እና፣ አንድነት ጎልቶ የሚታይበት በመሆኑ ይህንን በዓል ተሳቢ በማድረግ በከተማ አስተዳደር አጋር ድርጅቶች ከሃይማኖት ተቋማት ጋር እየተደረገ ያለው ድጋፍ ይበል የሚያሰኝ ተግባር በመሆኑ ተጠናክሮ መቀጠል እንደለበት ተናግረዋል።
በጎ በማድረግ የሚገኝውን የህልና እርከታና ደስታ በምንም የማይገኝ እንደሆነ ያስታወሱት አቶ ሙራድ በዚህ መልካም ተግባር ላይ የተሳተፉ አካላትን አመስግነዋል።
የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር. ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ አስራት ታደለ በበኩላቸው በከተማ ደረጃ የክረምት በጎ ፈቃድ ላይ በርካታ ወጣቶች በመሳተፍ ድጋፍ ለሚሹ አቅመ ደካሞችን በመርዳት የበኩላቸውን ሚና እየተወጡ ይገኛሉ ብለዋል ።
በወልቂጤ ከተማ አስተዳደር የሙሉ ወንጌል ቁጥር አንድ ቤተክርስቲያን አባል አቶ ቦጋላ ሃይሌ በበኩላቸው የከተማ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት የወጣቶች ዘርፍ ባለፉት በርካታ አመታት ከከተማ አስተዳደሩ ጎን በመቆም በማህበራዊ እና በኢኮኖሚያዊ ዘርፍ ላይ በርካታ አስተዋጽኦ ማድረጋቸውን ተናግረዋል ።
በተለይም ወጣቶች ማዕድ ማጋራት ፕሮግራሞችን በማዘጋጀት፣ በማረሚያ ተቋም ያሉ ታራሚዎች ካላቸው በማካፈል እና በሌሎችም ተግባራት ላይ በመሳተፍ የድርሻውን እየተወጡ መሆናቸውን አስረድተዋል ።
ድጋፍ የተደረገላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች በሰጡት አስታያየት ድጋፉ እንዳስደሰታቸው ተናግረዋል።
ዘጋቢ ፡ ደጋጋ ሂሳቦ-ከወልቂ-ጣቢያችን
More Stories
በተቋማትና በባለሙያዎች መካከል የውድድር መንፈስ በመፍጠር ቀልጣፋና ፈጣን አገልግሎት መስጠት እንደሚገባ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የቀቤና ልዩ ወረዳ አስተዳደር አስታወቀ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የጌዴኦ ዞን በ2017 ዓ.ም በመኸር እርሻ ከ24 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በተለያዩ ሰብሎች ለመሸፈን አቅዶ እየሠራ መሆኑን የዞኑ ግብርና መምሪያ አስታወቀ
”የምንተክላቸው ችግኞች ለትውልድ ተሻጋሪ ትሩፋትን የሚያስገኙ ናቸው” – ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ