በጎፋ ዞን የላሃ ከተማ አሰተዳደር  የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ ለአቅመ ደካሞችና ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች ማዕድ አጋርቷል

በጎፋ ዞን የላሃ ከተማ አሰተዳደር  የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ ለአቅመ ደካሞችና ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች ማዕድ አጋርቷል

የላሃ ከተማ ከንቲባ ክቡር አቶ አሸናፊ ጮራ በድጋፉ ማዕከል ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት ማዕድ ማጋራት መተሳሰብንና መተጋገዝን መሠረት በማድረግ ለወገኖቻችን ያለን ፍቅር የሚናሳይበት ተግባር መሆኑን ተናግረው ኃይማኖታዊ በዓላት የመደጋገፍ ፣ የመረዳዳትና የመተጋገዝ እሴቶቻችን መገለጫ ናቸው ስሉ ተናግረዋል ።

የተደረገው ድጋፍ በዓሉን ተደስተው እንዲያሳልፉ ታስቦ ሲሆን ከተደረገላቸው ድጋፍ የዓመት በዓል ስጋ ፣ የምግብ ዘይት ፣ ዱቄት ፣ ጨው እና አልባሳትም ይገኙበታል ።

የከተማው ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ከድር ሀሰን በበኩላቸው አቅመ ደካሞችና ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች እንዳይቸገሩ ታስቦ ድጋፍ እንደተደረገላቸው ገልጸው ብልጽግና ፓርቲ ሰው ተኮር ፓርቲ በመሆኑ አቅም የሌላውን በመደገፍ ፣ ማዕድ በማጋራት ፣ ቤት በመገንባት ፣ የተለያዩ በጎ ተግባራት ሲከናወን ቆይቷል ብለዋል።

ድጋፍ የተደረገላቸው ወገኖችም ከተማ አስተዳደሩ ላደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል ።

ዘጋቢ : አወል ከድር – ከሳውላ ጣቢያችን