የመተጋገዝ እና የአብሮነትን እሴቶችን በማሳደግ የጋራ ችግርን በጋራ መፍታት እንደሚገባ ተገለፀ
ይርጋዓለም ኮንስትራክሽን ድርጅት በሀዋሳ ከተማ ከ2ሺህ ለሚበልጡ አቅመ ደካሞች የማዕድ ማጋራት ስነ ስርዓት አካሄዷል ።
የሃይማኖት አባት የሆኑት አገልጋይ ወገኔ ተናኜ መደጋገፍ፣መረዳዳትና መፋቀር የሁሉም ሃይማኖት ቅዱሳት መፅሐፍት መሪ ሀሳቦች መሆናቸውን በመጥቀስ ያለው ለሌለው ማካፈልም ሃይማኖታዊ ግዴታ ነው ብለዋል።
ለመስጠት ቀና ልብ ያስፈልጋል ያሉት አገልጋዩ ነገር ግን ለጋሽ ለመሆን የግድ ሀብታም መሆን አይጠበቅም ብለው ይሄ በፈጣሪ የተወደደው ተግባር በብዙሃኑ ዘንድ መስፋፋት እና መለመድ አለበት ብለዋል።
ወይዘሮ ይርጋለም አስፋው ከይርጋዓለም ኮንስትራክሽን ድርጅት በማዕድ ማጋራቱ ወቅት እንደገለፁት ድርጅቱ ባለፉት 18 አመታት በአመት ሶስት ጊዜ ድጋፍ እያደረገ መዝለቁን ጠቅሰው ይሄም ተግባር ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
ለገና በዓልም የፊኖ ዱቄት ፣ዘይት ፣አልባሳት እና የንፅህና መጠበቂያ ሳሙናዎች ለአካል ጉዳተኞች እና ለድጋፍ ፈላጊዎች መከፋፈሉን ተናግረዋል ።
ድርጅቱ ለበርካታ ዜጎች የሲዳማ ክልልን ጨምሮ በተለያዩ የሀገሪቱ አከባቢዎች የስራ ዕድል መፍጠሩን ያነሱት ወይዘሮ ይርጋለም ማህበራዊ የሀላፊነት ግዴታውንም በትጋት ይወጣል ብለዋል።
የድጋፉ ተጠቃሚዎችም ለተደረገላቸው ሁሉ ምስጋና አቅርበዋል ።
ዘጋቢ : ጀማል የሱፍ
More Stories
ቆሻሻን በአግባቡ በማስወገድ ከተማዋ ፅዱና ውብ እንድትሆን የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ ነው – የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች በቋሚነት የሚደገፉበት ስራ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የቡርጂ ዞን አስተዳደር አስታወቀ
“አንድ ሰው ወደዚህች ምድር ሲመጣ እንዲሰራ የተፈቀደለትና የሚጠበቅበት ነገር አለ” – ታደሰ ገብሬ /ጃክሰን/