በመለሠች ዘለቀ
የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል ስናከብር ለምድራችን ሰላም በመጸለይና በመስበክ መሆን አለበት ሲሉ የሀይማኖት አባቶች ተናገሩ፡፡ የሀዋሳ ደብረ ጽዮን ቅድስት ኪዳነ ምህረት ቤተክርስቲያን ሰባኪ ወንጌል መምህር ታምራት ተስፋዬ እንዳሉት የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል ኢየሱስ ክርስቶስ የሰውን ልጅ ከሀጢአት ለማዳን በመንፈስ ቅዱስ ሀይል ከቅድስት ድንግል ማሪያም የተወለደበት እለት በመሆኑ በቤተ እምነቱ ልዩ ትርጉም አለው ብለዋል፡፡
በበዓሉ ወቅት ምዕመናኑ ልደቱን ሊገልጽ በሚችል ሁኔታ ነጭ ልብስ ለብሰውና ነጭ ተጎናጽፈው ወደ ቤተክርስቲያኗ በመምጣት በጸሎት፣ በቅዳሴና በስብአተ እግዚአብሔር የሚከበር ልዩ በዓል ነው ያሉት መምህር ታምራት ቅዳሴው ከተጠናቀቀ በኋላ ከለሊቱ 9 ሰዓት ላይ የገና ጾም እንደሚፈታ ተናግረዋል፡፡ በቤተ እምነቱ ቅዳሴውን በጋራ እንደሚቀድሱ ሁሉ በበዓሉ እለት ከአቅመ ደካሞች ጋር በጋራ ማዕድ መቋደስ ያስፈልጋል ያሉት የወንጌል ሰባኪው ድሆችን ማሰብ አንዱ የቤተ ክርስቲያኗ አስተምህሮት እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
ከሀይማኖት ሰው መሆን ይቀድማል ያሉት መምህር ታምራት ዘር ሀይማኖት ሳንል ከቤተ እምነት ውጪ ከተለያዩ ቤተ እምነቶች ፕሮቴስታንቶች፣ ካቶሊኮች እና ሙስሊሞች ለአቅመ ደካማ ወገኖች አስፈላጊ ቁሳቁሶችንና አልባሳት በመለገስ፣ እንዲሁም አብሮ በመብላት ማሳለፍ ይጠበቃል ሲሉ ተናግረዋል፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ ሲወለድ መልአክቶችም ክብር ለእግዚአብሄር በአርያም ይሁን፤ ሰላምም ለሰው ልጆች ሁሉ ተብሎ እንደተጻፈ በዓሉን ስናከብር ሰላምን አጥብቀን መፈለግና ለምድራችን ሰላም በመጸለይ ማክብር ይኖርብናል ሲሉም ነው መምህር ታምራት የተናገሩት፡፡
የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል እግዚአብሄር በአዳምና በሄዋን ውድቀት ምክንያት ከሰው ጋር ተለያይተው የነበረውን የጥል ግድግዳ ለማፍረስና መልሶ እርቅ ለማድረግ እግዚአብሄር ከእኛ ጋር ለመሆን ወደዚህ ምድር የመጣበትን እለት የምናስታውስበት በዓል ነው ሲሉ የኢትዮጵያ ወንጌላዊያን አብያተ ቤተ ክርስቲያን ህብረት ቦርድ ስራ አስፈጻሚና የሲዳማ ክልል የሐይማኖት ተቋማት ጉበኤ ስራ አስፈጻሚ አባል ፓስተር ሳሙኤል ቱንሲሳ ተናግረዋል፡፡ በመጽሀፍ ቅዱስ ላይ ህጻን ተወልዶልናል፤ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናል፤ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ነው ስሙም ድንቅ መካር ሀያል አምላክ የሰላም አለቃ ነው፤ ስለሚል በዓሉን ስናከብር ሰላምን ለሀገራችንና ለምድራችን በመስበክና ስለ ሰላም በመጸለይ ማሳለፍ አለብን ብለዋል፡፡
ኢየሱስ ማለት እግዚአብሔር ለአለም የሰጠው ስጦታ ነው ያሉት ፓስተር ሳሙኤል ምዕመኑ በዓሉን ሲያከብር መንፈሳዊንም ቁሳዊውን ስጦታ ለሌሎች በመስጠት መሆን አለበት ሲሉም ተናግረዋል፡፡
በኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ሀዋሳ ሀገረ ስብከት ሀዋሪያዊ አስተዳደር አባ ዮሐንስ ኑኜዝ በበኩላቸው በቤተ እምነቱ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በቅዳሴና በተለያዩ ሀይማኖታዊ ዝግጅቶች እንደሚከበር ጠቁመዋል። ኢየሱስ ክርስቶስ እኛን ከአብ ጋር ለማስታረቅ ከድንግል ማርያም የተወለደበት እለት በመሆኑ በዓሉን ስናከብር ስለ ሰላም በመጸለይና ከሰው ልጆች ሁሉ ጋር ሰላምንና ፍቅርን አጥብቀን የምንፈልግበት መሆን እንዳለበት አባ ዮሐንስ ተናግረዋል፡፡ ቦርድ ስራ አስፈጻሚና የሲዳማ ክልል የሐይማኖት ተቋማት ጉበኤ ስራ አስፈጻሚ አባል ፓስተር ሳሙኤል ቱንሲሳ ተናግረዋል፡፡
በመጽሀፍ ቅዱስ ላይ ህጻን ተወልዶልናል፤ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናል፤ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ነው ስሙም ድንቅ መከር ሀያል አምላክ የሰላም አለቃ ነው፤ ስለሚል በዓሉን ስናከብር ሰላምን ለሀገራችንና ለምድራችን በመስበክና ስለ ሰላም በመጸለይ ማሳለፍ አለብን ብለዋል፡፡ ኢየሱስ ማለት እግዚአብሔር ለአለም የሰጠው ስጦታ ነው ያሉት ፓስተር ሳሙኤል ምዕመኑ በዓሉን ሲያከብር መንፈሳዊንም ቁሳዊውን ስጦታ ለሌሎች በመስጠት መሆን አለበት ሲሉም ተናግረዋል፡፡
በኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ሀዋሳ ሀገረ ስብከት ሀዋሪያዊ አስተዳደር አባ ዮሐንስ ኑኜዝ በበኩላቸው በቤተ እምነቱ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በቅዳሴና በተለያዩ ሀይማኖታዊ ዝግጅቶች እንደሚከበር ጠቁመዋል። ኢየሱስ ክርስቶስ እኛን ከአብ ጋር ለማስታረቅ ቤተክርስቲያኗ በቋሚነት ድሆችን የመርዳት ልምድ ያላት መሆኑን የተናገሩት አባ ዮሐንስ በተለይም በዓላትን ምክንያት በማድረግ የተቸገሩ ወገኖቻችንን በማብላትና በማልበስ እንደሚያሳልፉ ተናግረዋል፡፡ እንኳን ለ2017 ዓ.ም የጌታችንና የመድሃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ የሚል መልዕክት ያስተላለፉት የሀይማኖት መሪዎቹ በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር፣ የበረከትና የደስታ እንዲሆን ምኞታቻውን በመግለጽ በምድራችን ላይ ስላሉ ግጭቶችና የተፈጥሮ አደጋዎች በመጸለይ በዓሉ መከበር እንዳለበት አሳስበዋል፡፡
More Stories
የገና ሰሞን በጉራጌ !!!
የወልቂጤ ከተማ የወንጌላዊያን አብያተ ክርስቲያናት ወጣቶች ህብረት ከወልቂጤ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ጋር በመተባበር የገናን በዓልን ምክንያት በማድረግ ለአቅመ ደካማ የህብረተሰብ ክፍሎች ድጋፍ አደረገ
በጎፋ ዞን የላሃ ከተማ አሰተዳደር የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ ለአቅመ ደካሞችና ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች ማዕድ አጋርቷል