የዘንድሮ የገና በዓል ገበያ መጠነኛ የዋጋ ጭማሪ ማሳየቱን የሀዋሳ ከተማ ሸማቾች ተናገሩ
ሀዋሳ፡ ታሕሣሥ 28/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) የዘንድሮ የበዓል ገበያ ሁኔታ ከወትሮ ተመጣጣኝ የዋጋ ጭማሪ ማሳየቱን የሀዋሳ ከተማ ሸማቾች ተናግረዋል፡፡
በሀዋሳ ከተማ በተለምዶ አሮጌ ገበያ ተብሎ በሚጠራው የንግድ ማዕከል ተገኝተን ያነጋገርናቸው ሸማቾች በምግብና ምግብ ነክ ሸቀጦች ላይ አንጻራዊ ጭማሪ አለ ብለዋል ፡፡
የበዓል ገበያዉ ካለፉት በዓላት ጋር ሲነፃፀር በተወሰነ ደረጃ ጭማሪ መኖሩን ሸማቾች ገልፀዋል፡፡
የገናን በዓል ምክንያት በማድረግ የዶሮ፣ ቅቤ፣ እንቁላል፣ የቀይ ሽንኩርትና ቅመማቅመሞች ዋጋቸው የጨመረ ሲሆን የነጭ ሽንኩርት ዋጋ እንዳልጨመረ ሸማቾቹ ተናግረዋል፡፡
በተመሳሳይ መልኩ ያነጋገርናቸው ነጋዴዎች በበኩላችው ለዛሬው የበዓል ገበያ ሙሉ ግብአቶችን ይዘው እንደቀረቡ ተናግረው ሕብረተሰቡ በተመጣጣኝ ዋጋ ሁሉም እንደአቅሙ የሚገበያዩበት ሁኔታ እንዳለ ጠቁመዋል፡፡
ዘጋቢ፡ ሐና በቀለ
More Stories
ታላቁ የህዳሴ ግድብ ተጠናቆ መመረቅን ምክንያት በማድረግ የይርጋጨፌ ወረዳ እና ከተማ አስተዳደር በጋራ በመሆን የድጋፍ ሰልፍ አካሄዱ
ሙያዊ ስነ-ምግባር የተላበሰ አገልግሎት በመስጠት የተገልጋዩን እርካታ ለማሳደግ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚገባ ተገለፀ
የካፋ ዞን ጤና መምሪያ የ2017 በጀት ዓመት አፈጻጸምና የ2018 ዕቅድ ዝግጅት ላይ ውይይት እያካሄደ ነው