የኢየሱስ ክርስቶስ የልደትና የጥምቀት በዓላትን ህብረተሰቡ በሰላማዊ መንገድ እንዲከበር አስፈላጊው ቅደመ ዝግጅት እየተደረገ ነው-የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ
በዓሉን አስመልክቶ እንደ ክልል በጸጥታ ዙሪያ የተደረጉ ዝግጅቶችን አስመልክቶ የቢሮ ሃላፊ አቶ ተመስገን ካሳ ለደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል ።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ሃላፊ አቶ ተመስገን ካሳ በመግለጫቸው እንዳስታወቁት በክልሉ የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላማዊ መንገድ እንዲከበር ቀደም ባሉ ዓመታት በተከበሩ በዓላት ላይ የነበሩ ጠንካራ ጎኖችንና ክፍተቶችን በመገምገም ማህበረሰቡን ያሳተፈ ዕቅድ ታቅዶ ወደ ስራ ተገብቷል ።
የጸጥታውን መዋቅር ዝግጅቶችን በተመለከተም እስከ ሚሊሺያ አካላት ድረስ የጋራ ግንዛቤ መሰጠቱን ገልጸዋል ።
በዓሉን ምክንያት በማድረግ ሰፊ ግብይት የሚፈጸም እንደመሆኑ የግብይት ስርዓቱ የሰዓት ገደብ ሳይጣል መገበያየት በሚያስችል መልኩ መታቀዱንም አቶ ተመስገን ተናግረዋል።
ህብረተሰቡ በባንኮች አከባቢና በግብይት ስፍራ በሚያደርጋቸውን እንቅስቃሴዎች ላይም ተገቢውን ጥንቃቄ ሊያደርግ ይገባል ያሉት አቶ ተመስገን በእነዚህ አካባቢዎችም የፀጥታ አካላት ጠንካራ ክትትል እንደሚያደርጉ ጠቁመዋል ።
በትራንስፖርት አካባቢ ከወትሮው በተለየ መልኩ ፍሰት ስለሚጨምር ህብረተሰቡ ሳይጉላላ የትራንስፖርት አገልግሎት ማግኘት እንዲችል ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን የገለጹት የቢሮው ኃላፊ አደጋዎች እንዳይከሰቱ የትራፊክ ፖሊሶች አሽከርካሪዎችና ህብረተሰቡ የድርሻቸውን ሊወጡ ይገባል ብለዋል ።
የቢሮዉ ኃላፊ አቶ ተመስገን በመጨረሻም በዓሉን አስመልክተው የመልካም ምኞት መግለጫቸውንም አስተላልፈዋል።
ዘጋቢ ፡ ተሻለ ከበደ -ከሆሳዕና ጣቢያችን

More Stories
የአፍላ ወጣቶችና ወጣቶችን የስነ ተዋልዶ ጤና ችግሮች ለመቅረፍ የተጀመሩ ጥረቶችን ለማጎልበት የጤና አደረጃጀቶችን ሚና ማሳደግ እንደሚገባ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ አስታወቀ
ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የመግባት ዕድል ያገኙ ተማሪዎች የበለጠ ውጤታማ ለመሆን ትምህርታቸው ላይ ብቻ ሊያተኩሩ እንደሚገባ መልዕክት ተላለፈ
የሀዲያ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ለ2018 በጀት ዓመት ከ10 ቢልዮን ብር በላይ በጀት ለተለያዩ የልማት ስራዎች እንዲውል በተገቢው እንደሚሠራ ገለፀ