የሶያማ ከተማ አስተዳደር የከተማ ግብርና ዩኒት በበኩሉ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን ችግሩን ለመቅረፍ እንደሚሠራ አስታውቋል።
የሶያማ ከተማ 01 እና 02 ቀበሌ ነዋሪ አቶ መሐመድ ጨርቆስ እና አቶ አሊ ሮጌ፤ በግማሽ ሄክታር መሬት ላይ ጥቅል ጎመን፣ ቲማቲም እና ሌሎች አትክልቶችን እያለሙ ቢሆንም የመስኖ ውሃ በበቂ ሁኔታ ወደአካባቢው አለመድረስና የዋግ በሽታ ፈተና እንደሆነባቸው ጠቁመው የሚመለከተው አካል ችግሩን እንዲፈታም ጠይቀዋል።
አቶ ሶካ ማሬ በበኩላቸው በአካባቢው ሽንኩርትና ጥቅል ጎመን እያለሙ ከዚህ በፊት ከለማው 2 መቶ ሺህ ብር እንዳገኙና የአሁኑም ጥሩ ደረጃ ላይ ያለ ቢሆንም የመስኖ ውሃ ቦይ ሳይጠናቀቅ በመቅረቱ የተፈለገውን ያህል ውሃ ስለማይደረስ መቸገራቸውን ተናግረዋል።
በቡርጂ ዞን ሶያማ ከተማ አስተዳደር የከተማ ግብርና ዩኒት መሪ አቶ መልጄ ሞሌ በበኩላቸው፤ እየተነሱ ያሉ ቅሬታዎች ተገቢ መሆናቸውንና በዩኒቱ አቅም ብቻ የሚፈታ ባለመሆኑ ከከተማ አስተዳደሩ እና በዞኑ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመነጋገር ችግሩን ለመፍታት እንደሚሠሩ ገልጸዋል።
ዘጋቢ፡ ቦጋለ ሉሳ – ከይርጋጨፌ ጣቢያችን
More Stories
ዲጂታል ኢትዮጵያን የመፍጠሪያ ጊዜን በማፋጠን ኢትዮጵያን የመጪው ዘመን መሪ ለማድረግ በትኩረት መስራት እንደሚገባ ተገለጸ
የሆሳዕና እናት ቃለ ህይወት ቤተክርስቲያን አዲሱን ዓመት ምክንያት በማድረግ ከአንድ መቶ በላይ ለሚሆኑ አቅመ ደካሞች የምግብ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገች
እመርታ ለዘላቂ ከፍታ!