ሀዋሳ፡ ታህሳስ 22/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) የሴቶች ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለእምርታዊ እድገት በሚል መርህ ቃል የኣሪ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት የሴቶች ሊግ በጂንካ ከተማ የጋራ ምክክር አድርገዋል፡፡
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ቢሮ ምክትል ኃላፊ ወይዘሮ ምህረት በላይ እንደገለፁት የሴቶች እኩልና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የበለፀገች ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ በሚደረገው ዘርፈብዙ እንቅስቃሴ ውስጥ ሴቶች የድርሻቸውን ሊወጡ ይገባል ብለዋል፡፡
ኃላፊዋ አክለው ሴቶች ያልተሳተፉበትና ተጠቃሚ ያልሆኑበት ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ እንቅስቃሴዎች ሁለንተናዊ ብልፅግናን ሊያረጋግጥ እንደማይችል ታምኖበት የሴቶች አደረጃጀት ላይ መንግሥት ትኩረት ማድረጉን ገልፀዋል፡፡
በአሪ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት የፖለቲካና የህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ኢያሱ ዘርፉ በበኩላቸው በዞኑ የሴቶችን ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቀሚነትን በማሳደግ እምርታዊ ለውጥ እንዲመጣ የሴቶችን አደረጃጀት በመጠናከር የሚደርስባቸውን ጫና ለመቀነስ እየተሠራ እንዳለም አብራርተዋል፡፡
የሴቶች ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በርካታ ሥራዎች መከናወኑን የሚገልፁት የአሪ ዞን ብልፅግና ፓርቲ የሴቶች ሊግ ፅህፈት ቤት ኃላፊ ይመኙሻል ተፈሪ በሴቶች ላይ የሚደርሱ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን በማስወገድ በትምህርታቸው ውጤታማ እንዲሆኑ እየተሠራ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
ሴቶች የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን በተደራጀ መንገድ ለመጠየቅና ተጠቃሚነታቸውን ለማረጋገጥ አቅም የሚፈጠር የጋራ ምክክር መደረጉን የመድረኩ ተሳታፊዎች አንስተው ለሴቷ ሁለንተናዊ ለውጥ የድርሻቸውን እንደሚወጡ ተናግረዋል::
ሴቶች በኢኮኖሚ፣ በጤና፣ በትምህርትና በለሎች ማህበራዊ ዘርፎች የሚደርስባቸውን ጫና ለመግታት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ሰነድ ቀርቦ በተሳታፊዎች ውይይት ተደርጓል፡፡
ዘጋቢ፡ ተመስገን አሰፋ – ከጂንካ ጣቢያችን
More Stories
ለህዳሴ ግድብ ቦንድ በመግዛት ለቀጣይ ትውልድ አሻራቸውን በማስቀመጣቸው ደስተኛ መሆናቸውን የዲላ ዙሪያ ወረዳ ነዋሪዎች ተናገሩ
የዲጂታል ስማርት ክፍል ተማሪዎችን ከዘመኑ ጋር ለማስተሳሰርና ተጨማሪ ትምህርት ቀስመው ውጤታማ እንዲሆኑ ታቅዶ ወደ ሥራ መገባቱን የወላይታ ዞን አረካ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት አስታወቀ
የዘንድሮው የጌዴኦ ብሔር የዘመን መለወጫ ዳራሮ በዓል በተለያዩ ኩነቶች መከበር ጀመረ