ህገወጥ ነጋዴዎችንና ደላላዎችን ከገበያ የማውጣት ተግባራት ተጠናክረው መቀጠላቸውንም ቢሮው በጋዜጣዊ መግለጫው አመላክቷል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ገለቦ ጎልቶሞ፤ የገናና ጥምቀት በዓላት ወቅት የምርት አቅርቦት ችግር፣ ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ፣ ህገ ወጥ ተግባራትን በመከላከል ህብረተሰቡ በተመጣጣኝ ዋጋ መሸመት እንዲችል ለማድረግ እየተሰራ እንደሚገኝ በመግለጫው አስታውቀዋል።
የፋብሪካ ምርቶች ለህብረተሰቡ በተመጣጣኝ ዋጋ እየቀረበ እንደሚገኝ የገለፁት ኃላፊው፤ ከእንስሳት ተዋጽኦ ጋር ተያይዞ ሻጩና ሸማቹ ብቻ መገበያየት እንዲችል ደላላዎችን ከገበያ የማውጣት ተግባራት እየተከናወኑ መሆናቸውን አመላክተዋል።
በኬላዎች አካባቢ ህገወጥ የቡና ዝውውር ችግርን ለመቅረፍ ትኩረት መሠጠቱን ገልፀው፤ ከነዳጅ አቅርቦት ጋር ተያይዞ እጥረት እንዳይኖር የክትትል ስራዎች ተጠናክረው መቀጠላቸውን አውስተዋል።
በዩኒየኖችና ማህበራት በኩል በክልሉ በ87 ከተሞች የፍጆታ ዕቃዎች እየቀረቡ ነው ያሉት ኃላፊው፤ ተጨማሪ የፋብሪካ፣ የኢንዱስትሪና የግብርና ምርቶች የማቅረብ ስራዎች እየተሰሩ ናቸዉ ብለዋል።
ህገ ወጥ ተግባራትን ከመከላከል አኳያ ግብረሃይል ተቋቁሞ የክትትልና ቁጥጥር ስራዎች እየተከወኑ መሆናቸውን አውስተው፤ አስፈላጊ እርምጃ እንዲወሰድም ሸማቹ ማህበረሰብ መጠቆም እንዳለበት አሳስበዋል።
ከማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ጋር በተያያዘ አበራታች ተግባራት በክልሉ መከናወናቸውን አብራርተዋል።
በክልሉ በ6 ማዕከላት የምግብ ዘይት እየተሰራጨ መሆኑን ገልፀው፤ የስኳር እጥረት እንዳይኖር ትኩረት መሠጠቱን በመግለጫቸው ገልጸዋል።
ዘጋቢ፡ እንጃ ገልሲሞ – ከአርባምንጭ ጣቢያችን

More Stories
የፍርድ ቤቶች እና የፍትህ ሴክተር መስሪያ ቤቶች ጥምረት የፍትህ አሰጣጥ ላይ ውጤታማ ማድረጉ ተገለጸ
አቶ ዮሐንስ አበጋ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሀዲያ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሆነው ተሾሙ
የአፈር ጤናን በመጠበቅና ለምነትን በማሻሻል የአርሶ አደሮችን ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ምርምር ኢኒስቲትዩት የወራቤ ግብርና ምርምር ማዕከል አስታወቀ።