ፍ/ቤቶች እና የፍትህ ተቋማት  በህገ መንግሥቱ የተሰጠውን  የዜጎች መብት በማክበር እና በማስከበር   የላቀ አስተዋጽኦ ማበርከት  ይጠበቅባቸዋል ተባለ

ፍ/ቤቶች እና የፍትህ ተቋማት  በህገ መንግሥቱ የተሰጠውን  የዜጎች መብት በማክበር እና በማስከበር   የላቀ አስተዋጽኦ ማበርከት  ይጠበቅባቸዋል ተባለ

ይህም የተባለው  በቡርጂ  ዞን የፍ/ቤቶች እና ፍትህ ተቋማት የአገልግሎት  አሰጣጥ  ለማሻሻል  ለሶስቱም  ወዋቅር አመራሮች  እና ባለድርሻ  አካላት በተዘጋጀ  የንቅናቄ  መድረክ   ላይ ነው።

በመድረኩ   ላይ  ንግግር ያደረጉት  የቡርጂ ዞን  ዋና አስተዳዳሪ   አቶ ዳኜ ህዶ  ፍርድ ቤቶች እና የፍትህ  ተቋማት  ለተገልጋዩ  ህብረ ሰብ  ፈጣን ፣ ግልፅ እና ታአማንነት ያለውን  አግልግሎት  መስጠት  እንዳለባቸውም   አሳስበዋል።

የቡርጂ   ዞን ከፍተኛ  ፍ/ቤት ፕሬዝዳንት  አሊ መሐመድ   በበኩላቸው  ፍ/ቤቶች  በህገ መንግሥት   የተሰጠውን የዜጎች መብት በማክበርና በማስከበር   የላቀ  አስተዋጽኦ ማበርከት  እንደሚጠበቅባቸው  ገልጸው  ለዚህም  እራሱን የቻለ ሪፎርም ተነድፎለት  ሀገራዊ ፣ ክልላዊና ዞናዊ  ሥራዎች  እንደተጀመሩ ተናግረዋል።

አክለውም  ሪፎርሙ ከህዝብ  ክንፍና ከባለድርሻ  አካላት የተሰበሰቡ ግብዓቶችን መነሻ እንዳደረገ ጠቅሰው  የቀድሞ  ማሻሻያ የተገመገመበት፣ የቀጣይ  የራዕይ፣ ተልዕኮ  እና ግብ  እንዲሁም  የክትትልና የግምገማ ሥርዓት የያዘ  መሆኑን  ገልፀዋል።

በውይይቱ  ላይ ከተሳተፉት  መካከል አቶ ወየሳ ወርቁ፣ አቶ አደን ማሬ እና ሌሎችም  በሰጡት  አስተያየት  በወይይቱ ላይ ከቀረበው  ሰነድ  ብዙ ግብዓት እንዳገኙና   እንደ ችግር የተነሱ ጉዳዮችን ለቅመው  በመውሰድ  ለማስተካከል  የበኩላቸውን  እንደሚወጡ  አንስተዋል።

ዘጋቢ : ቦጋለ ሉሳ ከይርጋ ጨፌ  ቅርንጫፍ ጣቢያችን