የሕዝብና የመንግስት ውስን ሀብት ለታለመለት ዓላማ በማዋል የዞኑን ልማት ለማፋጠን ባለድርሻ አካላት ከመቼዉም ጊዜ በላይ በቅንጅት መስራት አለባቸው – የጉራጌ ዞን ምክር ቤት
ሀዋሳ፡ ታህሳስ 21/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) የሕዝብና የመንግስት ውስን ሀብት ለታለመለት ዓላማ በማዋል የዞኑን ልማት ለማፋጠን ባለድርሻ አካላት ከመቼዉም ጊዜ በላይ በቅንጅት መስራት እንዳለባቸው የጉራጌ ዞን ምክር ቤት አስታወቀ።
የዞኑ ምክር ቤት የ2017 በጀት አመት የኦዲት ግኝት አስመላሽ ግብረ ሃይል የንቅናቄ መድረክ በወልቂጤ ከተማ ተካሂዷል።
የጉራጌ ዞን ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ አቶ ኸይሩ መሀመድ፤ ከ44 ሚልዮን ብር በላይ የኦዲት ጉድለት የታየ መሆኑን ገልጸው ይህም ከባለፈው በጀት ዓመት የተሸጋገሩና በተያዘው በጀት ዓመትም የታከለበት መሆኑን አስታውቀዋል።
በሁሉም መዋቅሮች የመንግስት እና የህዝብ ልማት ለማፋጠን የተመደበውን ውስን ሀብት ሳይባክን ለታለመለት አላማ ማዋል እንዲቻል በቅንጅት መስራት ይጠበቃል ብለዋል።
በተለያዩ የአሰራር ግድፈቶች ሆን ተብሎ ሃላፊነት በጎደለው ሁኔታ መፈጸም እና ሌብነት በስፋት እየታየ ነው ሲሉም ተናግረዋል።
የጉራጌ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ እና ግብርና መምሪያ ሀላፊ አቶ አበራ ወንድሙ፤ ግለሰቦች ያለ አግባብ የሚጠቀሙት ገንዘብ በየደረጃው ባለው የመንግት መዋቅር በጀቱ እየተቆጠረ እንደሆነ ገልፀው ችግሩን ለመቅረፍ በተደራጀ እና አሰራርን በጠበቀ መልኩ መምራት ይጠበቃል ሲሉም ተናግረዋል።
ለልማት የሚውለውን ውስን ሀብት የሚያባክኑ አካላትን ተጠያቂ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
ግብረ ሃይሉ በተገቢው ሀላፊነቱን ሊወጣ እንደሚገባ እንዲሁም በዞንና በወረዳ የተመደቡ ኦዲተሮች የጥራት እና የመረጃ ግልፀኝነት ችግር መፍታት ይጠበቃል ሲሉም አቶ አበራ አንስተዋል።
በዚህ መድረክ በአፈር ማዳበሪያ፣ በገቢዎች፣ በማዘጋጃ ቤት በኩል መሰብሰብ ያለባቸው የኦዲት ግኝት ላይ ግንዛቤ በመፍጠር እና የጉራጌ ዞን ፋይንስ መምሪያ በበጀት አመቱ የባለፉት ወራት ኦዲት ሪፖርት ቀርቧል።
በእነዚህ ግኝቶች ዙሪያም ውይይት ተደርጓል።
በውይይቱ የጉራጌ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት አቶ ሙዘኪር አወል፣ የዞኑ ፋይናንስ መምሪያ ሀላፊ አቶ አብዶ ሀሰን እና የሚመለከታቸው አካላት ስራውን በቅንጅት መምራት ይገባል ብለዋል።
የግንዛቤ ስራውን አጠናክሮ ከመስራት ባለፈ አጥፊዎችን በማረም የህግ የበላይነት ይከበራል ሲሉም አውስተዋል።
ዘጋቢ፡ እንዳልካቸው ደሳለኝ – ከወልቂጤ ጣቢያችን

More Stories
የአፍላ ወጣቶችና ወጣቶችን የስነ ተዋልዶ ጤና ችግሮች ለመቅረፍ የተጀመሩ ጥረቶችን ለማጎልበት የጤና አደረጃጀቶችን ሚና ማሳደግ እንደሚገባ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ አስታወቀ
ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የመግባት ዕድል ያገኙ ተማሪዎች የበለጠ ውጤታማ ለመሆን ትምህርታቸው ላይ ብቻ ሊያተኩሩ እንደሚገባ መልዕክት ተላለፈ
የሀዲያ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ለ2018 በጀት ዓመት ከ10 ቢልዮን ብር በላይ በጀት ለተለያዩ የልማት ስራዎች እንዲውል በተገቢው እንደሚሠራ ገለፀ