የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር በጎፋ ዞን በመሬት መንሸራተት አደጋ ጉዳት ለደረሰባቸው ተጎጂዎች በስምንት ሚሊየን ብር ወጪ የተገነባው የውሃ ፕሮጀክት ተመረቀ
በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር በጎፋ ዞን በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸው ዜጎች ማቋቋሚያ ፕሮጀክት አስተባባሪ አቶ አሰማ ግርማ እንደገለጹት፤ ማህበሩ ከጀርመን ቀይ መስቀል ማህበር ጋር በመተባበር በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ በመሬት መንሸራተት አደጋ ለተፈናቀሉ የኅብረተሰብ ክፍሎች ሁለት የውሃ ታንከርና ዘጠኝ የውሃ ቦኖዎችን አስገንብቶ ለምረቃ ማብቃቱን አስረድተዋል።
በዚህም 627 አባወራ ቤተሰብ የሆኑ ከ3 ሺህ በላይ ዜጎችን ተጠቃሚ ያደርጋል ብለዋል።
የጎፋ ዞን ቀይ መስቀል ማስተባበሪያ ጽ/ቤት አስተባባሪ አቶ ኢያሱ ጣሰው በበኩላቸው፤ የውሃ ግንባታው በስምንት ሚሊየን ብር የተከናወነ ሲሆን ከማህበሩ ድጋፍ በተጨማሪ ህብረተሰቡ 150ሺህ ብር የሚገመት የጉልበት አስተዋጽኦ ማድረጋቸውን አንስተዋል።
ማህበሩ ከጀርመን ቀይ መስቀል ማህበርና ከሌሎች አጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር ተጎጂዎችን በዘላቂነት ለማቋቋም እየሰራ መሆኑንም ጠቅሰዋል።
በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ዳንዳ
ማህበሩ ተጎጂዎችን በዘላቂነት ለማቋቋም ፕሮጀክት ቀርጾ ድጋፍ እያደረገ ሲሆን የቁሳቁስ፣ የገንዘብ እና ለምረቃ የበቃውን የውሃ ግንባታ ያካተተ ስለመሆኑ ተናግረዋል።
ተጎጂዎችን በዘላቂነት ለማቋቋም ማህበሩ ከክልሉና ከዞኑ መንግስት ጋር በቅንጅት እየሰራ መሆኑም ተናግረዋል።
በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ የተገኙት የጎፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ኢንጂነር ዳግማዊ አየለ የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር አደጋው ከተከሰተበት ዕለት ጀምሮ ለተጎጂዎች አስቸኳይ ሰብዓዊ እርዳታ ከማድረጉም በላይ ፣የገንዘብና የቁሳቁስ ድጋፍ ሲያደርግ መቆየቱን አስታውሰዋል።
አሁን ግንባታው ተጠናቆ ለአገልግሎት የበቃው የውሃ ፕሮጀክት የተጎጂዎችን የመጠጥ ውሃ ችግር በዘላቂነት የሚፈታ ስለመሆኑ አንስተው ማህበሩ ላደረገው ድጋፍ አመስግነዋል።
ካነጋገርናቸው የአከባቢው ነዋሪዎች መካከል አቶ ኤሊያስ በላይ እና ወ/ሮ ልዳየች ጉራዴ በሰጡት አስተያዬት የውሃ ተቋማቱ መገንባት የመጠጥ ውሃ ፍለጋ ረዥም ርቀት በመጓዝ የሚደርስባቸውን እንግሊት የሚያስቀርላቸው በመሆኑ መደሰታቸውን ገልጸዋል።
ዘጋቢ፡ አይናለም ሰለሞን – ከሳውላ ጣቢያችን
More Stories
የዜጎችን ሰላምና ደህንነት በዘላቂነት ለማረጋገጥ ከአጎራባች ክልሎች ጋር እየተሰሩ ያሉ ቅንጅታዊ ስራዎች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው ተገለጸ
የኤችአይቪ/ኤድስ ስርጭትን ለመከላከልና የተጣሉ ግቦችን ለማሳካት ትኩረት እንደሚያስፈልግ ተገለፀ
የጌዴኦን ብሔር ባህል፣ ቋንቋ እና የቱሪዝም መዳረሻ ሥፍራዎችን ለዓለም ለማስተዋወቅ እየተደረገ ባለው ጥረት ሁሉም ባለድርሻ አካላት የበኩቸውን እንዲወጡ የጌዴኦ ዞን አስተዳደር ገለጸ