የጌዴኦን ብሔር ባህል፣ ቋንቋ እና የቱሪዝም መዳረሻ ሥፍራዎችን ለዓለም ለማስተዋወቅ እየተደረገ ባለው ጥረት ሁሉም ባለድርሻ አካላት የበኩቸውን እንዲወጡ የጌዴኦ ዞን አስተዳደር ገለጸ

የጌዴኦን ብሔር ባህል፣ ቋንቋ እና የቱሪዝም መዳረሻ ሥፍራዎችን ለዓለም ለማስተዋወቅ እየተደረገ ባለው ጥረት ሁሉም ባለድርሻ አካላት የበኩቸውን እንዲወጡ የጌዴኦ ዞን አስተዳደር ገለጸ

የጌዴኦ ማህበረሰብ ቴሌቪዥን ጠቅላላ ጉባኤ ምስረታ በዲላ ከተማ እየተካሄደ ነው።

በጉባኤው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የጌዴኦ ዞን አስተዳዳሪ ዝናቡ ወልደ (ዶ/ር) ባለፉት ሰባት ወራት የጌዴኦ ማህበረሰብ ቴሌቪዥን ጣቢያ ሥርጭት ሥራ ለማስጀመር በርካታ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ሲሠሩ እንደነበሩ ገልጸዋል ።

እስካሁን በተሠሩ ሥራዎች 80 በመቶ የስቱዲዮ ግንባታ መጠናቀቁን ገልጸው በቀጣይ ሣምንት ከኢትዮ ሳት የሳታላይት ውል ስምምነት በማጠናቀቅ ለጌዴኦ ብሄር ዘመን መለወጫ የሙከራ ሥርጭት ለማስጀመር ትኩረት ሰጥተው እየሠሩ መሆናቸውን ተናግረዋል።

የጌዴኦ ማህበረሰብ ቴሌቪዥን ቀሪ ሥራዎች ተጠናቅቀው ወደ ሙሉ ስርጭት እስኪገባ ድረስ ምሁራን፣ የባህል ሽማንግሌዎች፣ እና ሁሉም ባልድርሻ አካላት የበኩላቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል።

አክለውም የግንባታ ሥራ ሂደት፣ ዶክመንተሪ ሥራ በመሥራት እና በጉዳዩ ዙሪያ ሃሳብ እና አስተያየት በመሥጠት የበኩላቸውን ለተወጡ ባለድርሻ አካላት ምስጋና አቅርበዋል ።

በጉባኤው ከኢፌዲሪ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ዶ/ር ኢንጂነር ስለሽ ኮሬ፣ ከደቡብ ኢትዮጵያ የክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት፣ የዞን እና ከከተማ መዋቅር የመጡ አስተባባሪ አካላት ፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የኃማኖት ተቋማት ተወካዮች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል ።

ዘጋቢ: እንግዳየሁ ቆሳ -ከይርጋጨፌ ጣቢያችን