ሀዋሳ፡ ታህሳስ 17/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) አባቶቻችን ያቆዩልንን የጀፎረ ባህላዊ አውራ መንገድ ጠብቆ ለትውልድ ማስተላለፍ እንደሚገባ የጉራጌ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ ገለፁ።
“ጀፎረ ባህላዊ የምህንድስና ጥበብ” በሚል መሪ ቃል የገጠር ኮሪደር ለማልማት የተዘጋጀ የንቅናቄ መድረክ በወልቂጤ ከተማ ተካሄዷል።
የኮሪደር ልማቱ አርሶ አደሩ ባህሉንና ወጉን ጠብቆ አካባቢውን ንጹህ ለኑሮ ተስማሚ በማድረግ ዘመናዊና ቀላል የአኗኗር ስልት እንዲከተል የሚያደርግ እንደሆነም ተገልጿል፡፡
በንቅናቄ መድረኩ ላይ የተገኙት የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ እንደገለፁት አባቶቻችን ያቆዩልንን የጀፎረ ባህላዊ አውራ መንገድ ጠብቆ ለትውልድ ማስተላለፍ ይገባል።
የኮሪደር ልማቱ አርሶ አደሩ ባህሉንና ወጉን ጠብቆ አካባቢውን ንጹህ፣ ጓሮውን በዶሮ፣ በአትክልትና ፍራፍሬ፣ እንዲሁም በማርና ወተት ምርት የተትረፈረፈ በማድረግ ዘመናዊና ቀላል የአኗኗር ስልት እንዲከተል የሚያደርግ እንደሆነም አቶ ላጫ ተናግረዋል፡፡
የጉራጌ ዞን ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ አለማየሁ ገብረ መስቀል በበኩላቸው ጀፎረን ከተለያዩ አደጋዎች ለመጠበቅ አባቶች ያስቀመጡትን መተዳደሪ ደንብ መተግበር ይገባል ሲሉ ጠቁመዋል።
የጉራጌ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ሃላፊ ወይዘሮ መሰረት አመርጋ ጀፎረ ለዘመናዊው የምህንድስና ጥበብ ፈር ቀዳጅ አስደናቂ የጉራጌ ባህላዊ አውራ መንገድ ነው ብለዋል።
ጀፎረ የተለያዩ ባህላዊ፣ ሃይማኖታዊ እና የሽምግልና ስርዓት የሚከናወንበት በርካታ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ግልጋሎቶችን እየሰጠ ይገኛል ብለዋል።
የመድረኩ ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት እንደ ሃገር እየተተገበረ ያለውን የገጠር ኮሪደር ልማት አርሶአደሩን በኢኮኖሚ የበለጠ ተጠቃሚ እንዲሆን የሚያስችል ነው ብለዋል።
የጀፎረ ይዘትን በጠበቀ መልኩ የገጠር ኮሪደር ልማት በተቀመጠለት ጊዜ ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል።
ዘጋቢ፡ አስቻለው አማረ – ከወልቂጤ ጣቢያችን

More Stories
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ግብርና ቢሮ ከግብርና ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በክልሉ ለሚገኙ የዘርፉ ባለሙያዎች ስልጠና መስጠት ጀመረ
የቅድመ በሽታ መከላከል ተግባራትን በአግባቡ በመፈፀም ጤናማ ትውልድ ለመፍጠር በሚደረጉ ጥረቶች ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ ተገለፀ
የሸዋል ዒድ (ቀሊ ፍቼ) ባህላዊ ስርዓት በስልጤ