ሀዋሳ፡ ታህሳስ 15/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) ለከተማ ዕድገትና ልማት ከመንግስት ብቻ ሳይሆን የህብረተሰቡ ተሳትፎ የጎላ ድርሻ እንዳለው በኮሬ ዞን የኬሌ ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ።
ለከተማዋ ልማትና ዕድገት ከመንግስት መጠበቅ ብቻ ሳይሆን ህብረተሰቡን በማሳተፍ የድርሻቸውን መወጣት እንደሚያስፈልግ የኬሌ ከተማ ነዋሪዎች ገልጸዋል።
የኮሬ ዞን ኬሌ ከተማ ከተመሠረተች በርካታ ዓመታትን እንዳስቆጠረች እና ገና ማደግ የሚገባትን ያህል እንዳላደገች የተናገሩት አንዳንድ የከተማዋ ነዋሪዎች፥ በከተማዋ ከበፊቱ ይልቅ አሁን ላይ የተጀመሩ የልማት ሥራዎች እንዳሉና ይህን ለማስቀጠል ደግሞ ሁሉም ህብረተሰብ ኃላፊነት አለበት ነው ያሉት።
ያለ ህብረተሰብ ተሳተፎ ልማትና ዕድገትን ማምጣት አይታሰብም የሚሉት ነዋሪዎቹ ሁሉም በሚችለው አቅም መደገፍና ለከተማዋ ዕድገት መረባረብ እንዳለበት ጠቁመው፥ አቶ ዮሐንስ ሽሎ፣ ወ/ሮ መሠረት ካሳ እና ሌሎችም የኬሌ ከተማ 02 ቀበሌ ነዋሪዎች እንደተናገሩት የሚሠሩ የልማት ሥራዎች ለህብረተሰቡ ጥቅም እንደሆነ የመንግስት አካላት ማወያየትና ግንዛቤ በመፍጠር በግልጸኝነት መሥራት ይጠበቅባቸዋል።
ዕድገትም ሆነ ልማት ከመንግስት ብቻ ከመጠበቅ ይልቅ የሚፈጠሩ ምቹ ሁኔታዎችን በመጠቀም ከተማችንን ውብና ጽዱ ለማድረግ የድርሻችንን መወጣት አለብን ሲሉ ያስረዱት ነዋሪዎቹ፥ ለከተማ ዕድገት መሳተፍና መሥራት ብቻ ሳይሆን የተሠሩትንና ገና የሚሠሩ የልማት ሥራዎችን በየኔነት ስሜት በመንከባከብ ለሚቀጥለው ትውልድ የማስተላለፍ ኃላፊነትም ጭምር አለብን ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
ዘጋቢ: ለምለም ኦርሳ – ከይርጋጨፌ ጣቢያችን
More Stories
በጎፋ ዞን መሎ ኮዛ ወረዳ በኮረሪማ ምርት ከሚለማው 8ሺህ 860 ሄክታር መሬት 50ሺህ ኩንታል ምርት ለማዕከላዊ ገበያ ለማቅረብ ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ እንደሚገኝ ተገለጸ
በደቡብ ኦሞ ዞን የዳሰነች ወረዳ የምሁራን ምክክር ተካሄደ
ምክር ቤቱ አረንጓዴ አሻራን የሚያጠናክር እና የተጎሳቆለ መሬትን እንዲያገግም የሚያስችል አዋጅ አፀደቀ